Monday, September 28, 2015

ሁለት የሶማሌ የጦር አውሮፕላኖችን መተው የጣሉት የቀድሞ አየር ኃይል ጀግና አረፉ

የኮለኔል ባጫ ሁንዴ የህይወት ታሪክ

ኮለኔል ባጫ ሁንዴ በአንቦ አካባቢ በጊንጪ ከተማ ተወለዱ ።በአምቦ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ በ1965 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በኢትዮጵያ አየር ሃይል በአውሮፕላን ጥገና አገራቸውን ለማገልገል ተቀጥረው ስልጠናቸውን እንደጨረሱ ከክፍላቸው ያመጡት ውጤት የላቀ በመሆኑ እና የተዋጊ አውሮፕላን በራሪ ለመሆን ባሳዩት ከፍተኛ ፍላጎት ሙያው የሚጠይቀውን ማንኛውንም መስፈርት በማሟላት ወደ በረራ ትምህርት ቤት ገቡ።Colonel Bacha Debele
የሚፈለግባቸውን የበረራ ትምህርት እንደጨረሱ ወደ ተዋጊ ስኳድሮን በመመደብ የኤፍ 86 አውሮፕላን ሲበሩ ቆይተው የኢትዮጵያ አየር ሃይል F-5E የሚባል አዲስ አውሮፕላን ሲገዛ ወደ አሜሪካን አገር ተልከው በዚሁ አውሮፕላን ስልጠና በመውሰድ እና በማጠናቀቅ ወደ አገራቸው ተመልሰው በወቅቱ አገራችንን የወረሩትን የሱማሌ ወራሪዎች ጋር ፍልሚያ ውስጥ በመግባት በአየር ላይ ውጊያ ሁለት የሱማሌ ሚግ አውሮፕላኖችን መትተው የጣሉ ሲሆን በዚህም ላሳዩት ከፍተኛ ጀግንነት ከኢትዮጵያ መንግስት የጦር ሜዳ የላቀ ጀግንነት ሜዳይ ተሸላሚ ሆነዋል።

ኮለኔል ባጫ በወቅቱ በነበረው የኢትዮጵያ መንግስት አስተዳደር ባለመደሰት በ1986 ሲሲና የምትባል አውሮፕላን በማብረር ወደ ሱዳን ተሰደው በመጨረሻም ወደ አሜሪካ በመምጣት በሳንፍራንሲስኮ ከተማ ህይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስ ኖረዋል።
ኮለኔል ባጫ የአንድ ሴት እና የሁለት ወንዶች አባት ሲሆኑ ሶስት የልጅ ልጅ ለማየትም በቅተዋል።
የቀድሞው አየር ሃይል ማህበር በዋሽንግተን ዲሲ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እየተመኘ በመኮንኑ እረፍት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ይገልፃል።

No comments:

Post a Comment