Saturday, September 5, 2015

ኡጋንዳ በሶማሊያ ከሚገኙ የሰላም አስከባሪ ሰራዊት አባላት 12ቱ ተገድለውባት ብሄራዊ ሀዘን ተቀምጣለች።

Adjama Dejene's photo.

ኡጋንዳ በሶማሊያ ከሚገኙ የሰላም አስከባሪ ሰራዊት አባላት 12ቱ ተገድለውባት ብሄራዊ ሀዘን ተቀምጣለች። የተገደሉት ወታደሮቿ አስክሬናቸው በአውሮፕላን ተጭኖ መዲናይቱ ሲገባ በከፍተኛ የሀዘን ፕሮግራም ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ በመውለብለብ ክብር ተደርጎላቸዋል። ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የሚመራው መንግስት ለኢትትዮጵያውያን ይህን ክብር ነፍጓል። በ3ወር ውስጥ ከ100 በላይ የኢትዮጵያ ልጆች በማይመለከታቸው ጦርነት ደማቸው ፈሷል። ሬሳቸው በመንገድ ላይ እንደ ውሻ ተጎትቷል። እስከአሁን ግን አንድ ወታደር ስለመገደሉ በህወሀት በኩል ለህዝብ አልተገለጸም። ወጉም ይቅር። ክብሩም ይነፈግ። የሀዘን ቀን ግድየለም ቅንጦት ይሁንብን። ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ አይበል። ምናለ አንድ የህወሀት መንግስት ባለስልጣን ወጥቶ ይሄን ያህል ወታደር ተገደለብን ብሎ ቢገልጽ? አንድ ወቅት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በሶማሊያ ስላለቁት የኢትዮጵያ ልጆች በምክር ቤት ተጠይቀው ”ይሄ የምክር ቤቱ ስልጣን አይደለም። የመግለጽም ግዴታ የለብንም” ማለታቸው ይታወሳል።
መሳይ መኮንን
Adjama Dejene's photo.

No comments:

Post a Comment