Tuesday, September 15, 2015

አልሸባብ ሁለት ወንድማማቾችን ሰላይ ነበሩ በማለት በአሰቃቂ ሁኔታ ገደለ

መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በማዕከላዊ ሶማሊያ ሂራን ግዛት ራሶ መንደር አቅራቢያ የ20 ና የ25 ዓመት ወጣት የሆኑት ወንድማማቾች ሶማልያዊያንና አንድ ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ በአልሸባብ ታጣቂዎች በግፍ ተገለው ተገኝተዋል።

ሁለቱ ወንድማማቾች ባለፈው ሳምንት ነበር በቡቃበል ከተማ ውስጥ በድንገት የኢትዮጵያ ወታደሮችና የሶማሊያ መንግስት ሰራዊቶች አካባቢውን ለቀው ሲወጡ በአልሸባብ ሚሊሻዎች ታግተው የተያዙት። የአካባቢው ነዋሪዎች እማኝነታቸውን ሲሰጡ እንደተናገሩት አልሸባብ የኢትዮጵያና የሶማሊያ ወታደሮች ለቀው ሲወጡ ሁለቱን ወንድማማቾች ለኢትዮጵያና ለሶማሊያ ብሔራዊ ጦር ትሰልላላች በማለት በአሰቃቂ ሁኔታ እንደገደሉዋቸው አስረድተዋል።
የሶማሊያ ባለስልጣናት በተጨማሪ እንደገለጹት የአፍሪካ ሕብረት የሰላም አስከባሪ ጦር እጅ የነበሩት ኤልሳንዲ እና ኮንትርዋሪ ከተሞች በአሁኑ ወቅት በአልሸባብ እጅ መግባታቸውንና በአፍሪካ ህብረት ተሽከርካሪ ላይ የቦንብ ጥቃት መፈጸሙን ቪኦኤ አክሎ ዘግቧል።

No comments:

Post a Comment