Thursday, June 7, 2018

የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ቡድን የደጋፊዎች ማህበር፣ በደጋፊቻቸው ላይ የሚደርሰው እንግልት እንዲቆም ጠየቀ።

(ኢሳት ዜና ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ/ም)ማህበሩ የፋሲል ከነማ መለያ ልብስን በመልበሱ ምክንያት ወልቃይት ላይ የታሰረውን ፍቃዴ አሰፋን የአባልነት መታወቂያ አያይዞ “ለሚመለከተው ክፍል” በሚል ርዕስ በላከው ደብዳቤ፣ የክለቡ ደጋፊ የክለቡን መለያ በመልበሱ እና መታወቂያ በመያዙ ምክንያት የደረሰበትን እስርና እንግልት ነቅፏል። ፍቃዱ አሰፋ- የፋሲል ከነማ ማልያን በመልበሱ ወልቃይት ላይ መታሰሩንና የኮማንድ ፖስት አባላት ነን ያሉ የህወሃት መኮንኖች፣ ማንነትን መሰረት ያደረገ ስድብ እንደሰደቡት ተዘግቦ ነበር። የእግር ኳስ ክለቡ የደጋፊዎች ቡድን ወጣት ፈቃዴ የቡድኑ የብር ደረጃ አባል መሆኑን አክሎ ገልጿል።

No comments:

Post a Comment