Friday, June 15, 2018

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዢን ዶክተር ይናገር ደሴ ሊተኳቸው ይችላሉ ተባለ

Image may contain: 1 person(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 8 /2010) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዢ የሆኑትን አቶ ተክለውልድ አጥናፉን የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽነሩ ዶክተር ይናገር ደሴ ሊተኳቸው እንደሚችሉ ተዘገበ።
በአዲስ አበባ የሚታተመው ሳምንታዊ የቢዝነስ ጋዜጣ አዲስ ፎርቹን እንደዘገበው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለብሔራዊ ባንክ ገዢነት ዶክተር ይናገር ደሴን ይሾማሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀም ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ተወስኗል።
ሆኖም አቶ በቃሉ ዘለቀ ከንግድ ባንክ ፕሬዝዳንትነት ተነስተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ ሊሆኑ እንደሚችሉም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ምንጮችን በመጥቀስ አዲስ ፎርቹን ዘግቧል።
ኢሳት የውስጥ ምንጮችን በመጥቀስ የብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ እንዲነሱ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መወሰኑን መዘገቡ ይታወሳል።
በአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አይኤምኤፍ ውስጥ የአፍሪካ ሃላፊ የሆኑት አቶ አበበ አዕምሮ ሥላሴ ለብሔራዊ ባንክ ገዢነት መጠየቃቸውን ሆኖም ባሉበት ሃላፊነት ሳቢያ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን በኢሳት መዘገቡም አይዘነጋም ።
የብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዢ ዶክተር ዮሃንስ አያሌው ቀደም ሲል ከስልጣን መነሳታቸው ይታወሳል

No comments:

Post a Comment