Tuesday, June 19, 2018

በአርጎባና የኦሮሞ ብሔረሰብ ተወላጆች መሃከል በተፈጠረ ግጭት ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት ደረሰ

 (ኢሳት ዜና ሰኔ 12 ቀን 2010 ዓ/ም) በሰሜን ሸዋ ዞን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አሞራ ቤት ቀበሌ በአርጎባ ማህበረሰብ ተወላጆችና በፈንታሌ ወረዳ ውስጥ በሚኖሩ የከረዩ ማህበረሰቦች መካከል ከመሬት ጋር በተያያዘ በተነሳ ግጭት የሰዎች ህይወት አለፈ። ትናንት በነበረው ግጭት ቢያንስ የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉንና 7 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የአካባቢው ናሪዎች ተናግረዋል። ግጭቱ አንድ ህጻን መገደሉን ሰበብ አድርጎ የተነሳ ቢሆንም፣ የኦሮምያ ልዩ ሃይል አባላት በግጭቱ ሳይሳተፉ እንዳልቀረ የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ። የሰሜን ሸዋ ዞን የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ተፈራ ግጭት መነሳቱና የሰዎች ህይወት ማለፉ ትክክል ቢሆንም፣ ከኦሮምያ ባለስልጣናት ጋር ባደረጉት ውይይት የኦሮምያ ልዩ ሃይል መሳተፉን ለማረጋገጥ እንዳልቻሉ ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment