Monday, June 11, 2018

በባህርዳር ዩኒቨርስቲ የሆሊስቲክ ፈተና አንፈተንም ያሉ የምህንድስና ተማሪዎች ተቃውሞ አሰሙ

(ኢሳት ዜና ሰኔ 4 ቀን 2010 ዓ/ም) ተማሪዎቹ ተቃውሞ ያሰሙት ለ2011 ዓም የሆልስቲክ ፈተና ተፈታኞች የወጣውን ማስታወቂያ በመቃወም ነው። የቴክኖሊጂ ተቋሙ ባወጣው ማስታወቂያ፣ ማንኛውም ተማሪ ከሆልስቲክ ፈተና በፊት የሚሰጡትን ሁሉንም የት/ት አይነቶች ሳያጠናቅቅ ፈተናውን መውሰድ የማይችል መሆኑን እንዲሁም ማለፊያ ውጤት 50 እና ከዚያ በላይ ያመጣ ተማሪ ብቻ ወደ ኢንተርንሽፕ መውጣት ወይም ትምህርቱን መከታተል የሚችል መሆኑን ይገልጻለ። ተማሪዎቹ ሆልስቲክ ፈተና መመዘኛ ሳይሆን ተማሪውን መቀነሳ ነው ብለዋል። በተበላሸ ምግብ፣ በተበላሸ አሰራር፣ በተበላሸ መሳሪያ፣ ሃቅም በሌላቸው መምህራን ተምረን አንባረርም ብለዋል።

No comments:

Post a Comment