Friday, June 15, 2018

በየአካባቢው የተፈጠረው ግጭት የለውጥ ሂደቱ ባልተዋጠላቸው አካላት ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 8/2010) በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በየአካባቢው የተፈጠረው ግጭት በሀገሪቱ የተጀመረው የለውጥ ሂደት ባልተዋጠላቸው አካላት ጠንሳሽነት እየተመራ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግስት ገለጸ።
የፌዴራል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት የመንግስትን አቋም በሚያመለክተው መግለጫው እንዳለው አካባቢያዊ ወሰንና ሌሎች መሰል ምክንያቶችን መነሻ በማድረግ ለግጭት የሚያነሳሱ ሴራዎች እየተስተዋሉ ይገኛሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለምበአዋሳ የተጀመረው ግጭት ግድያን ዘረፋን ጨምሮ ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በወላይታ ሶዶ ግድያውን በማውገዝ በተካሄደ ትዕይንተ ህዝብ ላይ ስዎች ተገድለዋል።
በተያያዘ ዜና ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ክልል ተወላጆችን በአጭር ጊዜ ወደ ቦታቸው ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገረሳ ገለጸዋል፡፡
የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ እንዳለው በግጭቱ የተሳተፉትን አካላት መርምሮ ርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት ተደርጓል።
በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ የተፈጠረው ግጭት በሃገሪቱ የተጀመረው የለውጥ ሂደት ባልተዋጠላቸው አካላት ጠንሳሽነት እየተመራ መሆኑን ነው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት የገለጸው።

ጽሕፈት ቤቱ የመንግስትን አቋም በሚያመለክተው መግለጫው እንዳለው አካባቢያዊ ወሰንና ሌሎች መሰል ምክንያቶችን መነሻ በማድረግ ለግጭት የሚያነሳሱ ሴራዎች እየተስተዋሉ ይገኛሉ።
ይህን መሰል ጥፋትና ግጭት ያቀነባበሩት እና ሁከቱን ያባባሱት አካለት ዓላማ አሁን በአገሪቱ የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም ማወክ ነው ብሏል።
የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት መግለጫ እንዳለው በኢትዮጵያ እየተገነባ ያለውን አገራዊ አንድነት ለመናድና በአጠቃላይ በሀገሪቱ የትጀመረውን ለውጥ ለማደናቀፍ እየተሞከረ ነው። እናም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ድርጊቱ ሊታገለው ይገባል ነው ያለው።
ይህ በእንዲህ እንዳለም በአዋሳ የተጀመረው ግጭት ግድያን ዘረፋን ጨምሮ ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በወላይታ ሶዶ ግድያውን በማውገዝ በተካሄደ ትዕይንተ ህዝብ ላይ ስዎች ተገድለዋል። በተያያዘ ዜና ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ክልል ተወላጆችን በአጭር ጊዜ ወደ ቦታቸው ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገረሳ ገለጸዋል፡፡
ሀላፊነታቸውን መወጣት እየተገባቸው ለዜጎች መፈናቀል ምክንያት በሆኑ አመራሮች ላይም ርምጃ መወሰዱን አቶ ለማ ተናግረዋል፡፡
በተያያዘ ዜና የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኪሽን ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር ነገሬ ሊንጮ ከኦሮሚያ ክልል ከተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ጋር ለመወያየት ወደ ባህርዳር እንደሚያመሩ ተነግሯል።
በኦሮሚያ ክልል የኦህዴድ ማእከላዊ ኮሚቴ በቅርቡ ባከሄደው ስብሰባ ከ2ሺህ በላይ የዞን የወረዳና የቀበሌ አመራሮች ሲባረሩ ከ 540 ባላይ የሚሆኑት ደግሞ ከደረጃቸው ዝቅ እንዲሉ ተደርገዋል።

No comments:

Post a Comment