Tuesday, June 26, 2018

በአሶሳ ብሄርን ማእከል ባደረገ ጥቃት 3 ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዜና ሰኔ 19 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ከሳምንት በፊት በስልጣን ላይ የነበሩ የህወሃት አባላት በብሄር ብሄረሰቦች መካከል ግጭት እንዲፈጠር ለማድረግ በርታና ጉምዞች በአማራ እና ኦሮሞ ተወላጆች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም አስደርገው 3 ሰዎች መሞታቸውንና ከ20 ያላነሱ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። የህወሃት ሰዎች በአካባቢው እንደነበሩ እና ባምባሲና እና አሶሳ ዙሪያ እየዞሩ የበርታ ልጆቹን ሲቀሰቅሱ እንደነበር ነዋሪዎች ተናግረዋል። ጥቃቱ ትናንት እንዲፈጸም የተደረገው ዛሬ ለዶ/ር አብይ የተጠራውን የድጋፍ ሰልፍ ለማደናቀፍ እንደበር እነዚሁ ምንጮች ገልጸዋል። አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የተወሰነ ጉዳት እንደደረሰበት፣ የተወሰኑ ባጃጅ መኪናዎች እንደተሰባበሩና እስከ 3 ሰኣት ድረስ ወደ አዲስ አበባና ሌሎችም አካባቢዎች የሚካሄደው የትራንስፖርት ፍሰት ተቋርጦ እንደነበር ነዋሪዎች ገልጸዋል። አሁንም በአካባቢው ውጥረት እንዳለ ታውቋል።

No comments:

Post a Comment