Thursday, June 28, 2018

በተደራጀ ሁኔታ ሽብር የሚፈጽሙ፣ መብራትና የቴሌኮም ኔትወርክ የሚያጠፉ፣ የኢኮኖሚ አሻጥር በመፈጸም የኑሮ ውድነት እንዲፈጠር የሚያደርጉ ኃይሎች መኖራቸውን መንግስት አስታወቀ

(ኢሳት ዜና ሰኔ 21 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የጀመሩትን አገራዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ለማስተጓጎል በተደራጀ ሁኔታ የሚሰሩ ኃይሎች መኖራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት አስታወቀ። እነዚህ ቡድኖች በአዲስ አበባው የድጋፍ ሰልፍ ከተፈጸመው የቦንብ ጥቃት በተጨማሪ መብራትና የቴሌኮም ኔትወርክ ማጥፋት፣ የኢኮኖሚ አሻጥር በተደራጀ አኳኋን በመስራት የኑሮ ውድነት በአገሪቱ እንዲባባስ እና የተለያዩ ህዝባዊ አገልግሎቶችን እንዲሰጡ የተቋቋሙ ተቋማት አስፈላጊውን አገልግሎት እንዳይሰጡ እያደረጉ እንደሚገኙ ለማረጋገጥ መቻሉንም ጽ/ቤቱ አመልክቷል፡፡ ይህን ሕገወጥ ድርጊት የሚፈጽሙ አካላትን አጣርተው ለሕግ የሚያቀርቡ ኮሚቴዎች መቋቋማቸውንና ውጤቱንም ለሕዝቡ በወቅቱ እንደሚገለጽ መግለጫው አትቷል። ሕዝቡ ከኮሚቴዎቹ ጎን በመቆም አጥፊዎችን ለፍርድ ለማቅረብ በሚደረገው ሂደት ላይ ተባባሪ በመሆን የአገሪቱን ሰላም ለማስጠበቅ ዘብ እንዲቆም ጥሪ ቀርቧል።

No comments:

Post a Comment