Thursday, June 7, 2018

ከሶማሊያ ወደ የመን በጀልባ በማቋረጥ ላየ የነበሩ 46 ኢትዮጵያውያን መሞታቸውን አይኦኤም አስታወቀ

ዓለምአቀፉ የስደተኛ ጉዳዮች ማኅበር አይኦኤም እንዳስታወቀው ፤ በሕገወጥ አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ከቦሳሶ ሶማሊያ ወደ የመን ለማሻገር 100 ኢትዮጵያውን ስደተኞችን አሳፍሮ የነበረ ጀልባ ማክሰኞ ዕለት በመገልበጡ አደጋው ደርሷል።
በጀልባው ላይ 83 ወንዶችና 17 ሴቶች የነበሩ ሲሆን ተስፋ አድርገው ሲጓዙ የነበረው የመን ደርሰው ሥራ ለማግኘት ነበር። የተገለበጠው ጀልባ ኢትዮጵያኖች ብቻ የተሳፈሩበት በመሆኑ 46 ሲሞቱ 16ቱ ደግሞ የገቡበት አልታወቀም ተብሏል።

No comments:

Post a Comment