Wednesday, January 17, 2018

በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት የብረታ ብረት አምራች ፋብሪካዎች ሊዘጉ ነው የአገሪቱ ባንኮች ምንዛሬ የማቅረብ አቅማቸው ተሟጧል

 በውጭ ምንዛሬ ተገዝተው ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ጥሬ እቃዎችን ለመግዛት የሚያስችል የውጭ ምንዛሬ በአገሪቱ በመጥፋቱ ፋብሪካዎች ካለ ምርት ፆማቸውን ውለው ለማደር ተገደዋል። በተለይ በብረታ ብረት ምርት ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶች የውጭ ምንዛሬ ማግኘት የሰማይ ያህል እንደራቃቸውና የውጭ ምንዛሬ ዶላር ለማግኘት ባንኮችን ደጅ ለመጥናት መገደዳቸውን የኮተቤ ብረታ ብረት ድርጅት ባለክሲዮን አቶ አሰግድ ማሞ አስታውቀዋል።
አብዛሃኞቹ በመስኩ የተሰማሩ ባለሃብቶች ጥሪታቸውን አፍስሰው የገነቧቸው ፋብሪካዎችን ታቅፈው በጥሬ ዕቃ አቅርቦት እጥረት ምክንያት እጃቸውን አጣምረው ለመቀመጥ መገደዳቸውን ባለሃብቶቹ ገልጸዋል። ሕጋዊ ባለሃብቶች ምንዛሬ አጥተው ባሉበት ሁኔታ ግን አንዳንድ ባለሃብቶች በሕገወጥ መንገድ ምንዛሬ እንዲያገኙ ይደረጋል ብለዋል። ከውጭ በማስገባት ጤናማ ፉክክር እንዳይኖር ተደርጓል። ነገርግን አንዳንድ ባለሃብቶች ያሉዋቸውን አስመልክቶ ድርጅቶቹ እነማን እንደሆኑ በዝርዝር ከመግለጽ ግን ተቆጥበዋል።

አቶ አሰግድ ማሞ ''የጥሬ ዕቃ አቅርቦት እጥረት የተፈጠረው በውጭ ምንዛሬ አለማግኘት ችግር ነው፡፡ ይህ ባለመሆኑ የፋብሪካዎቻችን የማምረት አቅም ተዳክሟል፡፡ በዚህ ሳቢያም በሚሊዮን የሚቆጠር ኪሳራ እያጋጠመን ነው፡፡ መንግሥት ለብረት አምራቾች ለጥሬ ዕቃ ማስገቢያ የውጭ ምንዛሬ ይሰጣል የሚባል ጭምጭምታ ቢሰማም እስከአሁን ያገኘነው ነገር የለም፡፡ አሁን ያለን ጥሬ ዕቃ በጣም አነስተኛ ነው፡፡ በአጭር ጊዜ የውጭ ምንዛሬ አግኝተን ጥሬ ዕቃ ከውጭ ማስገባት ካልቻልን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ፋብሪካው ለማቆም ይገደዳል፡፡ ጉዳዩን ለመንግሥት ብናሳውቅም እንደ አገር የውጭ ምንዛሬ እጥረት መኖሩ ተገልፆልን አርኪ ምላሽ አላገኘንም'' ብለዋል።
ኢትዮ ቴሌኮምና የኤሌክትሪክ ኃይልን ጨምሮ የመንግስት ተቋማት ብረትና ብረት ነክ ውጤቶችን ከአገር ውስጥ አምራቾች መግዛት ሲገባቸው ከውጭ መግዛታቸው በባለሃብቶች ላይ ቅሬታን እንደፈጠረባቸው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ዘግቧል።
የኢትዮጵያውያን የጋራ ግብረሃይል በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ ዘመዶቻቸው የሚልኩትን ገንዘብ በህጋዊ ባንኮች በመላክ የገዢውን ፓርቲ እድሜ እንዳያራዝሙ የተዓቅቦ ዘመቻ መጥራቱ ይታወሳል። አገዛዙ አብዛኛውን የውጭ ምንዛሬ ገቢ የሚያገኘው ኢትዮጵያውያን ለዘመዶቻቸው ከሚልኩት ገንዘብ ነው።

No comments:

Post a Comment