Monday, January 29, 2018

መረጃ
በወልድያ ተቃውሞው ቀጥሎአል። የአጋዚ ወታደሮች አስላቃሽ ጭስ በመበተን ሰልፈኛውን ለመበተን ሞክረዋል። ይሁን እንጅ ተቃውሞው እንደቀጠለ ነው። የቀበሌው ጽፈት ቤት ተቃጥሎአል። መንገዶች በመላ ተዘጋግተዋል።
በጎብዬ ህዝብን ለመሰብሰብ የሞከረው የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ያለው አባተ፣ በሽማግሌዎች እርዳታ ተርፎ ከከተማ እንዲወጣ ተደርጓል። 
በመርሳ ወታደሮች ተሰብስበው በነበረበት ወቅት በተወረወረ ፈንጅ 18 ወታደሮች ጉዳት ደርሶባቸዋል። 16 ወታደሮች ህክምና አግኝተው ከሆስፒታል ሲወጡ፣ ሁለት ወታደሮች ግን በጽኑ ቆስለው ወልድያ ልዩ ክትትል በሚደረግበት ክፍል ውስጥ ተኝተዋል። 
የአርበኞች ግንቦት7 የሰሜን እዝ ከወልድያ ጀምሮ ባሉት ከተሞች፣ “ተነሱ” የሚሉ የጥሪ ወረቀቶችን መበተኑን ወረቀቶችን ያነበቡ የአይን እማኞች ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment