Wednesday, January 31, 2018

በምስራቅ አፍሪካ በቂ ምግብ ካላገኙት 5 ሚሊዮን ህጻናትና እርጉዝ ሴቶች መካከል ከ60 በመቶ በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ናቸው

በምስራቅ አፍሪካ በቂ ምግብ ካላገኙት 5 ሚሊዮን ህጻናትና እርጉዝ ሴቶች መካከል ከ60 በመቶ በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ናቸው
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ክፍል አስተባባሪ ግብረሃይል ባወጣው ሪፖርት ባለፈው አመት በአፍሪካ ቀንድ በቂ ምግብ ካላገኙት 5 ሚሊዮን 200 ሺ ህጻናትና እርጉዝ ሴቶች መካከል 3 ሚሊዮን 600 የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ናቸው። 
በአፍሪካ ቀንድ 5 ሚሊዮን 5 መቶ ሺ ዜጎቭ በተለያዩ ምክንያቶች ሲፈናቀሉ፣ 1 ሚሊዮን 400 የሚሆኑት ደግሞ ስደት ጠያቂዎች ናቸው። 
14 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች የምግብ እጥረት ያጋጠማቸው ሲሆን፣ በዚህ አመትም የምግብ እጥረቱ ተባብሶ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

No comments:

Post a Comment