Wednesday, January 24, 2018

የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች በሰሜን ኢትዮጵያ (አማራ ክልል) ተደጋጋሚ ጥቃቶችን እየፈጸሙ ነው



የአግ7 አርበኞች በህወሓት ሎጆስቲክ አቅርቦት ላይ ጥቃት ፈፀሙ ፡፡
ጥር 15 ቀን 2010 ዓ/ም ከቀኑ 11:40 ሲሆን በሰሜን ወሎ ዞን ሀራ ከተማ በኩል ለህወሓት መከላከያ 12ተኛ ክፍለ ጦር አገልግሎት የሚውል አንድ ቤንዝን ነዳጅ የጫነ ቦቴ ከነ ተሳቢው እና አንድ አሱዚ መከና ደረቅ ረሽን የጫነ ተሽከርካሪ በደፈጣ ይጠብቁት በነበሩ አርበኞች በተፈፀመበት ጥቃት ሙሉ በሙሉ ነዷል ፡፡ በአሁኑ ሰዓት በአካባቢው ውጥረት የነገሰ ሲሆን ወደ ትግራይ የሚወስደው መንገድ ዝግ ነው ፡፡ ህወሓት ለጊዜው በአፋር በኩል መጠቀምን ቢመርጥም የአፋር ሕዝብ ቁጣ በማሳየቱ በተለይም በወልዲያ ንፁሀንን ዜጎች እየገደሉ በዚህ ማለፍ ክልክል ነው በማለት መንገድ እየዘጋ ይገኛል ፡፡ በተያያዘ ዜና ያለ ክልሉ እውቅና ከትግራይ ተንቀሳቅሶ ወደ ወልዲያ በመግባት ጅምላ ጭፍጨፋ የፈፀመው የህወሐት መከላከያ ጉዳይ ዛሬም አወዛጋቢ ሁኖ ቀጥላል ፡፡
ድል የህዝብ ነው! !
የአግ7 የሰሜን ኢትዮጵያ ዕዝ! !

-------------------------------------------
ጥር 15 ቀን 2010 ዓ/ም ከምሽቱ 2:05 ሲሆን በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን መተማ ከተማ አስተዳደር ንብረትነቱ የህወሓት የደህንነት አባል የሆነው ጉዕሽ በላይ የተባለው ንብረት አዲስ ዘመን ሆቴል ተብሎ በሚጠራው ላይ ከፍተኛ የህወሓት ወታደራዊ እና የደህንነት ሰዎች እንዲሁም የካብኔ አባላት በተገኙበት የራት ግብዣ እንዳላቸው ቀድሞ መረጃ የደረሳቸው ሃይሎች በዚህ ቦርደር አካባቢ በሚገኝ ከተማ እና ከፍተኛ ወታደራዊ ጥበቃ በሚደረግበት ቦታ በድፍረት በመግባት በቁጭት በፈፀሙት የቦንብ ጥቃት በሆቴሉ ውስጥ ውስኪ እየተራጩ ፡ ጮማ እየቆረጡ ፡ ሲጨፍሩ በነበሩ አመራሮች ላይ በተወሰደ እርምጃ 2 አመራሮች ወዲያውኑ ሲሞቱ ሊሎች 5 አመራሮች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል ፡፡
ወልዲያ ላይ ጥር 12 እና 13 ቀን 2010 ዓ/ም የጥምቀት በዓልን ለማክበር በወጡ ንፁሀን ዜጎች ላይ የጅምላ ጭፍጨፉ ፈፅመው ገና 2 እና 3 ቀን ሳይሆነው የፈሰሰው ንፁሀን ደም ሳይደርቅ የህወሓት ሰዎች ምንም ሞራል የሊላቸው ውስኪ እየተራጩ ጮማ እየቆረጡ ሲጨፍሩ ማየት እጅግ ዘግናኝ ድርጊት በመሆኑ ይህን ጥቃት ሊፈፅሙ ችለዋል ብለዋል ምንጮቻችን ፡፡ በመሆኑም የንፁሀንን ደም ለመጥረግ እና በገዳዬች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ወልዲያ ድረስ መሔድ አያስፈልግም በአቅራቢያችን ዘረኞች እና አረመኔዎች በንፁሀን ደም እጃቸው የተጨማለቁ ስላሉ በነሱ ላይ እርምጃ በመውሰድ የነፃነት ጊዜያችንን እናቀርባለን ብለዋል ። ጥሪም አስተላልፈዋል የንፁሃን ደም ለመመለስ ወልዲያ ድረስ መሄድ አያስፈልግም ትግል ባቅራቢያችን ነው ያለው ስለዚህ ሁሉም በያለበት ትግሉን ሊቀላቀል ይገባል ብልዋል ።
ዝርዝር ሁኔታውን እየተከታተልን እንገልፃለን ፡፡
ድል ለሕዝብ !!!
የአግ7 የሰሜን ኢትዮጲያ ዕዝ ፡
--------------------------------------------
አሁን የደረሰን ዜና ፡፡
ቀደም ሲል በሰበር ዜና በገለፅነው መሰረት ጥር 15 ቀን 2010 ዓ/ም ምሽት ላይ በመተማ ከተማ በተወሰደው እርምጃ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው የህወሓት የደህንነትና የካቤኔ አባል ስም ዝርዝር የደረሰን ሲሆን በዚህ መሰረት ፡፡ ሃዱሽ የተባለው በሰሜን ምዕራብ ቀጠና በምዕራብ ክፍል የድንበር አካባቤ የደህንነት ኃላፊ የሆነው እና ሙሌጌታ የተባለው የመተማ ከተማ አስተዳደር የካብኔ አባል እና የከተማው የፀጥታ ዘርፍ ኃላፈፊ እንዴሁም የኩማንድ ፖስቱ ተጠሪ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ጎንደር ዩኒቨርስቲ ሪፊራል ሆስፒታል ተልከው ማንቂያ (ሪከቨሪ) ክፍል ተኝተው ይገኛሉ ፡፡
ሁኔታውን አሁንም እየተከታተልን እንገልፃለን ፡፡
የአግ7 የሰሜን ኢትዮጵያ ዕዝ ፡፡

No comments:

Post a Comment