Wednesday, January 17, 2018

የሙስሊሞች የመቃብር ቦታ ይከበርልን ጥያቄው መልስ ባለመሰጡ የከሚሴ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ገለጹ

የሙስሊሞች የመቃብር ቦታ ይከበርልን ጥያቄው መልስ ባለመሰጡ የከሚሴ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ገለጹ
በከሚሴ ከተማ የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች የመቃብር ስፍራቸው የቆሻሻ መጣያ በመሆኑ እንዲከበርላቸው ጥያቄ አቅርበዋል።
ከአሁን በፊት በተደረጉ ህዝባዊ ስብሰባዎች ችግሩ መኖሩን በተደጋጋሚ ገልጸው የከተማው አስተዳደር መፍትሄ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም ምንም አይነት ምላሽ ሳያገኙ መቆየታቸውን ቅሬታ አቅራቢዎች ተናግረዋል፡፡
በእስልምና እምነት በመቃብር ላይ መጸዳዳትና ቆሻሻ መጣል የተከለከለ 'ሃራም' (ሀጢያት) መሆኑን የሚያነሱት ቅሬታ አቅራቢ ፤የከተማ አስተዳድሩ ለእስልምና ተከታዩ ማህበረሰብ መስጠት ያለበትን ክብር አልሰጠም ይላሉ፡፡

መስኖ ፣አባ ካራና የመሳሰሉት የቀብር ቦታዎች በከፍተኛ ደረጃ በቆሻሻ የተሞሉና የመጸዳጃ ቦታ በመሆናቸው በተደጋጋሚ ለከተማ አስተዳደሩ በማመልከት አጥር እንዲደረግና እንዲከበር ጥያቄውን ቢያቀርቡም፣ መልስ የሚሰጣቸው አካል ማግኘት እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡
ቅሬታ አቅራቢ የሙስሊም ማህበረሰቡ ተወካዮች እንደሚናገሩት ከዞኑ እስልምና አመራሮች ጋር በመነጋገር አካባቢውን ለመጠበቅ በሚያስችል መልኩ መስጊድ እንዲሰራ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
ለዚህም አስፈላጊ የሆነውን በዙሪያው የሚገኙትን የአስልምና ተከታዮች ፊርማ በማሰባሰብ ቢያቀርቡም መስተዳድሩ ግን 'ጆሮ ዳባ' በማለት ለዓመታት ምላሽ መነፈጋቸው እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል፡፡

No comments:

Post a Comment