Wednesday, January 3, 2018

ፖለቲካ እስረኞች መፈታት ለሰብአዊ መብት መከበር ጥሩ ጅምር ቢሆንም ወንጀል ፈጻሚዎች ሳይጠየቁ የሚያመልጡበት እንዳይሆን አምነስቲ ጠየቀ

ፖለቲካ እስረኞች መፈታት ለሰብአዊ መብት መከበር ጥሩ ጅምር ቢሆንም ወንጀል ፈጻሚዎች ሳይጠየቁ የሚያመልጡበት እንዳይሆን አምነስቲ ጠየቀ
ታዋቂው የሰብአዊ መብት ድርጅት፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መግለጫ የፖለቲካ እስረኞች ይፈታሉ መባሉ በኢትዮጵያ ለሰብአዊ መብት መከበር አዲስ ምዕራፍ መከፈት ሊሆን ይችላል ብሎአል።
እስረኞቹ ቀድሞውንም መታሰር አልነበረባቸው የሚለው ድርጅቱ፣ ወሳኔው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ላይ ተግባራዊ እንዲሆን ጠይቋል። የጸረ ሽብር ህጉን ጨምሮ ሌሎች አፋኝ ህጎችም እንዲሰረዙ አምነስቲ ጠይቋል።
ለአመታት ስቃይ መፈጸሚያ ካምፕ ሆኖ ሲያገለግል የቆየው ማእከላዊ እስር ቤት እንደሚዘጋ መነገሩ መልካም ቢሆንም፣ በግቢው ውስጥ ሲፈጸም የነበረውን ወንጀል ለማንጻት መሆን እንደሌለበትም ድርጅቱ አስታውሷል። በአገሪቱ ሲፈጸሙ የቆዩት ወንጀሎች በሙሉ ምርመራ ተደርጎባቸው ወንጀለኞች በጥፋታቸው የሚቀጡበት አሰራር ሲፈጠር ብቻ የሰብአዊ መብት መከበር እድል ይኖራል ያለው አምነስቲ፣ ከ1983 ዓም ጀምሮ አድራሻቸው የጠፉ ዜጎች ላይ ምርመራ ማድረግና መግለጽ እንደሚገባም ድርጅቱ አስታውቋል።

No comments:

Post a Comment