Tuesday, October 3, 2017

የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መፍትሄ አጥተው እየተሰቃዩ ነው

(ኢሳት ዜና–መስከረም 23/2010) የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መፍትሄ አጥተው እየተሰቃዩ ነው
ከአጠቃላይ ፈተና ጋር በተያያዘ የባህርዳር ዩኒቨርስቲ የምህንድስና ተማሪዎች ያሰሙትን ተቃውሞ ተከትሎ ምግብ እና መጠለያ በመከልከላቸው ሌሊቱን በቤተክርስቲያንና በሰዎች ቤት ተጠግተው መሳለፋቸውን ተማሪዎች ተናግረዋል።
የዩኒቨርስቲው ባለስልጣናት ተማሪዎች ፈተና አንፈተንም እንዳሉ አድርጎ በአማራ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ መስጠታቸው ተማሪዎችን አሳዝኗል። ተማሪዎች እስከ ዛሬ ሲሰራበት የነበረው አሰራር መቀየሩን የሰሙት ለፈተና ሊቀመጡ የተወሰኑ ቀናት ሲቀራቸው በመሆኑ አሰራሩ በቂ ውይይት ሳይደረግበት ተግባራዊ መሆኑን ይቃወማሉ።
የዩኒቨርስቲው ፕ/ት ዶ/ር ባይሌ ዳምጤ አሰራሩ መቀየሩን ቢያምኑም ፣ ከተማሪዎች ጋር ዩኒቨርስቲው ተወያይቶ መፍትሄ ለምን እንዳላስገኘ ከአማራ መገናኛ ብዙሃን ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ “ይህ እኮ ዩኒቨርስቲ ነው” የሚል መልስ ሰጥተዋል።

ዩኒቨርስቲው ከተማሪዎች ጋር ለመወያየት ያልፈቀደው አንድም “አልሸነፍም” በሚል አሰስተሰብ፣ ሌላም ባጋጣመው የገንዘብ እጥረት የተነሳ ሊያባርራቸው ስለፈለገ ሊሆን እንደሚችል ተማሪዎች አስተያየታቸውን ይሰጣሉ።
300 የሚሆኑ ተማሪዎች አቦ ቤተክርስቲያን ውስጥ በፖሊስ ተከበው ማደራቸውንም ገልጸዋል። የባህርዳር ከተማ ህዝብ አንዳንድ ድጋፎወችን በማድረግ ላይ መሆኑንም ተማሪዎች ተናግረዋል።
4ኛ አመት የኢንጂኒሪንግ ተማሪዎች ለፈተና ቀድሞው እንዲገኙ የተደረገ ሲሆን፣ የ2ኛ እና 3ኛ አመት ተማሪዎች በሚቀጥለው ሳምንት ትምህርት ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

No comments:

Post a Comment