Wednesday, October 18, 2017

በብአዴን ፅ/ ቤት ላይ ወታደራዊ ጥቃት አድርሰዋል የተባሉ ግለሰቦች የ"ሽብር" ክስ ተመሰረተባቸው በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ንፋስ መውጫ ከተማ በሚገኝ የብአዴን ፅ/ ቤት ላይ ወታደራዊ ጥቃት አድርሰዋል የተባሉ ግለሰቦች የ"ሽብር" ክስ ተመስርቶባቸዋል።

(ኢሳት ዜና ጥቅምት 08 ቀን 2010 ዓም) በብአዴን ፅ/ ቤት ላይ ወታደራዊ ጥቃት አድርሰዋል የተባሉ ግለሰቦች የ"ሽብር" ክስ ተመሰረተባቸው
በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ንፋስ መውጫ ከተማ በሚገኝ የብአዴን ፅ/ ቤት ላይ ወታደራዊ ጥቃት አድርሰዋል የተባሉ ግለሰቦች የ"ሽብር" ክስ ተመስርቶባቸዋል። ትናንት ጥቅምት 7/2010 በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት ተከሳሾች ክሱ ተነቦላቸዋል።
በእነ ፈለቀ አባብዬ የክስ መዝገብ ስር የተከሰሱት ፈለቀ አባብዬ፣ ዋሴ ታደሰ፣ ፈንታሁን አበበና ገደፋዬ ሲሆኑ ፈለቀ አባብዬ፣ ዋሴ ታደሰ እና ገደፋዬ የአርበኞች ግንቦት 7 አባል በመሆን፣ አባላትን በመመልመል፣ መሳርያና ሌሎች ቁሳቁሶችን መግዧ የሚሆን ገንዘብ በመቀበል ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። በተጨማሪም ከዋና ሳጅን አገኘሁ አቻው ጋር ግንኙነት በመፍጠር ስማዳ፣ ስቴ እና ጋይንት አካባቢ ወታደራዊ ቤዝ
በማፈላለግ፣ ከሰሜን ጎንደር ለሚመጡ አባላት ስልጠና በማመቻቸትና ለሌሎች አባላትም የፖለቲካ ስልጠና ሰጥተዋል በሚል በማሴር፣ በማቀድና በመዘጋጀት የሽብር ወንጀል ተከሰዋል። በሌላ በኩል አቶ ፈንታሁን አበበ "ለሽብርተኝነት" ድጋፍ መስጠት የ"ሽብር ወንጀል" ክስ ቀርቦበታል።
በተመሳሳይ ዜና ደግሞ በሽብር ወንጀል የተከሰሱት የዋልድባ መነኮሳት በደል እየደረሰባቸው ነው።
በእነ ተሻገር ወልደሚካኤል የክስ መዝገብ የሽብር ክስ የቀረበባቸው የዋልድባ መነኮሳት የሆኑት አባ ገ/ እየሱስ ኪ/ ማርያም እና አባ ገብረስላሴ ወልደ ሀይማኖት ቂሊንጦ እስር ቤት ውስጥ በደል እየደረሰባቸው እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። መነኮሳቱ ከሌላ ሰው ጋር እንዳይነገገሩ እቀባ የሚደረግባቸው ሲሆን እየመከራችሁ ነው፣ ቅስቀሳ ታደርጋላችሁ በሚል ወከባ እና ማስፈራሪያ እንደሚፈፀምባቸው ታውቋል። ከእነሱ ጋር የሚያወራ እስረኛም ማስፈራሪያና ዛቻ ይደርስበታል ተብሏል። መነኮሳቱ ፀሎት ሲመሩና ፀበልም ለእስረኛው ሲሰጡ የነበረበት ጊዜ ነበር። ሆኖም አሁን ፀሎትና ፀበል በመከልከሉ እስረኛው ጥያቄ ሲያቀርብ " ፀበልኮ ውሃ ነው። ከፈለክ ሻወግ ገብተህ ታጠብ። ይህን ማን እንደሚያዘጋጀው እና ለምን እንደሚዘጋጅ እናውቃለን" በሚል እምነታቸውንም ማንቋሸሻቸውን ለማወቅ ተችሏል። በተለይ በሌላ ወንጀል የታሰሩ እስረኞችን " እነሲ ሽብርተኞች ናቸው። ከእነሱ ጋር አትቅረቡ።" በሚል በክሳቸው እንደሚያሸማቅቋቸው ተነግሯል።
መነኮሳቱ ከሌሎች እስረኞች ጋር ምግብ እንዳይመገቡ፣ ለእነሱ የመጣን ምግብ ለሌላ እንዳይሰጡ ወይንም ሌላ ያመጣውን ምግብ እነሱ አብረው እንዳይመገቡ ክልከላ ተደርጎባቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ በእየ እስር ቤቱ እስረኞችን ለመሰለል የሚታሰር የደህንነት አባል ከጎናቸው እንዲተኛ በማድረግ ክትትል እየተደረገባቸው ነው ተብሏል። መነኮሳቱ በእምነታቸው ላይ ጫና እየተሰረገባቸው በመሆኑ፣ ከሌሎች ጋር አብረው እንዳይውሉና እንዳይነጋገሩ መደረጉን እና አጠቃላይ የሚፈምባቸውን ወከባ በተጨማሪ ጨለማ ቤት እናስገናችኋለን የሚል ማስፈራሪያ ደርሷቸዋል።
እነሱም ሆነ ሌሎች የዞን 2 እና 3 እስረኞች ሌሊት እየተጠሩ እንደሚደበደቡም የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

No comments:

Post a Comment