Monday, October 9, 2017

በምስራቅ አፍሪካ አድማሱን እያሰፋ የመጣውን የርሃብ አደጋን ለመዋጋት የግብረ ሰናይ ድርጅቶች የጋራ ትብብርብ ያስፈልጋል ሲል ተመድ አስጠነቀቀ

በኢሊኖ የአየር መዛባት በተከሰተ የርሃብ አደጋ እና በእርስበርስ ጦርነቶች ምክንያት የአያሌ የምስራቅ አፍሪካ ዜጎች የመኖር አጣብቂኝ ውስጥ መግባታቸውን ተመድ አስታውቋል። በኢትዮጵያ፣ ኬኒያ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን የሚኖሩ ለምግብ እጥረት የተጋለጡ አፋጣኝ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው 24 ሚሊዮን ዜጎች ይገኛሉ።
በቀጠናው በተከሰተው ድርቅ እና የጸጥታ መደፍረስ ምክንያቶች 15 ሚሊዮን የሚሆኑ ታዳጊ ሕጻናት ከምግብ እጥረት በተጨማሪ ለጤና እክሎች ተጋላጭ ሆነዋል። ከእነዚህ ውስጥ በግምት ቁጥራቸው ከ800 ሽህ በላይ የሚሆኑ ሕጻናት ለከፋ የርሃብ አደጋ መጋለጣቸውንና በተለይ አርብቶ አደሮች የቤት እንስሳቶቻቸው በድርቁ በማለቃቸው ችግሩን ይበልጥ አወሳስቦታል።
ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ በደቡብ እና ምስራቅ ኢትዮጵያ ድርቁ አድማሱን እያሰፋ የመጣ ሲሆን 8.5 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን የእለት ተእለት የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። በኢትዮጵያ እስካሁንም የተጠበቀውን ያህል ዝናብ ባለመዝነቡ ከችግሩ ለመውጣት የነበረው ተስፋ ተመናምኗል። የርሃብ ተጠቂው ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችልና ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ ሊፈጠር ይችላል ሲል ተመድ አስጠንቅቋል።
በኬኒያ 3.4 ሚሊዮን ዜጎች እለታዊ የምግብ ረድኤት ጠባቂ ዜጎች ያአሉ። በተመሳሳይ በሶማሊያ 6.2 ሚሊዮን ዜጎች የርሃብ ተጋላጭ መሆናቸውን ሪሊፍ ዌብ ዘግቧል።
(ኢሳት ዜና መስከረም 28 ቀን 2010 ዓም)

No comments:

Post a Comment