Tuesday, October 10, 2017

የምንዛሬ ለውጡን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ለመጨመር ጥናት እየተደረገ ነው

በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ የዶላር እጥረት ማጋጠሙን ተከትሎ አገዛዙ የምንዛሬው ለውጥ ለማድረግ ውሳኔ ካሳለፈ በሁዋላ በነዳጅ የመሸጫ ዋጋ ላይም ከፍተኛ ጭማሪ ለማድረግ የሚያስችል ጥናት እየተጠና ነው።
ከጥቅምት 1 ቀን 2010 ዓም ጀምሮ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ26 ብር ከ93 ሳንቲም ይመነዘራል። እስከዛሬ 23 ብር በመያዝ አንድ ዶላር ይገዛ የነበረ ሰው፣ ከጥቅምት 1 ጀምሮ በ26 ብር ይገዛል። የብር የመግዛት አቅም መዳከም፣ አሁን የሚታየውን የኑሮ ውድነት ይበልጥ ያባብሰዋል ተብሎ ተሰግቷል። ብሄራዊ ባንክ የምንዛሬ ለውጡ የወጭ ንግዱን በማበረታታት የውጭ ምንዛሬ በበቂ ሁኔታ እንዲገኝ ያደርጋል የሚል መግለጫ ሰጥቷል።
የውጭ ምንዛሬ ለውጡን ተከትሎ በነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ለማድረግ የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት ጥናቱን አጠናቆ ጨርሷል። (ኢሳት ዜና–መስከረም 30/2010)

No comments:

Post a Comment