Wednesday, October 18, 2017

የኔዘርላንድስና የቤልጂየም መንግስታት የጉዞ ማስጠንቀቂያ አወጣ

(ኢሳት ዜና ጥቅምት 08 ቀን 2010 ዓም) የኔዘርላንድስና የቤልጂየም መንግስታት የጉዞ ማስጠንቀቂያ አወጣ
የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ከሁለት ሳምንት በፊት ባወጣው እና እስከዛሬ ባጸናው ውሳኔው ወደ ኢትዮጵያ የሚሄዱ ዜጎቹ በተለይ ወደ ሶማሊ እና ኦሮምያ ክልል እንዳይጓዙ አስጠንቅቋል።
በመላ አገሪቱ ተቃውሞዎች በመካሄድ ላይ መሆናቸውንም የሆላንድ መንግስት ገልጿል።
የቤልጂየም መንግስትም እንዲሁ ወደ ኢትዮጵያ የሚሄዱ ዜጎቹ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጠይቋል። በአዳማ፣ አምቦ፣ አርሲ ነገሌ፣ ድሬዳዋ፣ ሃረር፣ ሻሸመኔ እና ወሊሶ እንዲሁም ሞጆ እና ሃዋሳ ፣ በጅማና አዲስ አበባ እና ሌሎችም አካባቢዎች ሲደረጉ ተቃውሞዎች ሲደረጉ እንደነበር በማስታወስ ዜጎቹ እንቅስቃሴያቸውን እንዲገቱ መክሯል።

በኢትዮጵያ ሶማሊ እና ኦሮምያ አካባቢዎች በተለይም የባሌ ተራሮችን ለመጎብኘት ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ጉዞአቸውን እንዲያስተካክሉ ፣ ወደ ድሬዳዋ፣ ሃረር እና ጅጅጋ ከተሞችም እንዳይጓዙ መክሯል።
ዜጎቹ ወደ ጋምቤላ፣ ሶማሊ፣ ሱርናም፣ እንደሁም ኢትዮጵያን በሚያዋስኑት ጅቡቲ፣ ኤርትራ፣ ኬንያ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን አካባቢዎች በሚገኙ የኢትዮጵያ ከተሞች ምንጊዜም መጓዝ እንደሌለባቸው አሳስቧል።
በሌላ በኩል የአሜሪካ መንግስት ባወጣው መግለጫ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ የሚታዩት ተቃውሞዎች በሰላም መጠናቀቃቸውን ብናደንቅም አሁንም በርካታ ተቃውሞወች በግድያ መጠናቀቃቸው እንዳሳዘነው ገልጿል። እነዚህ ግድያዎችና የሃይል እርምጃዎች በገለልተኛ ወገን እንዲጣሩም የአሜሪካ መንግስት ጠይቋል።
የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ህዝቡ ተቃውሞውን በሰላም እንዲገልጽ እንዲፈቅዱ የአሜሪካ መንግስት ጠይቋል።

No comments:

Post a Comment