Monday, June 6, 2016

በኦሮምያ የፖሊስ አዛዦች ለአስቸኳይ ጉዳይ በሚል ተጠሩ


ግንቦት ፳፱(ሃያ ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለማእረግተኛ የፖሊስ አዛዦች በሙሉ ለአስቸኳይ ሰትራቴጂ ለውጥና የፖለቲካ ጉዳይ በሚል ለ3 ወራት ቆይታ ደብረዘይት በሚገኘው መከላከያ ግቢ እንዲገቡ ተደርገዋል።

የፖለቲካ እና የስትራቴጂ ለውጡ ምን እንደሆነ ለማወቅ ባይቻልም፣ አዛዦቹ ከስልጠና በሁዋላ ማእረግ ተደርቦላቸው በመከላከያ አስተዳደር ስር የሚገኘውን የማረጋጋት ሚና ሃላፊነት ይሰጡዋቸዋል።

በኦሮምያ ያለው የህዝብ ተቃውሞ እንደገና ማገርሸቱ መንግስትን ስጋት ላይ መጣሉን ምንጮች ይገልጻሉ

No comments:

Post a Comment