Monday, June 13, 2016

ብአዴን የደረሰበትን ወቀሳ ተከትሎ ለነባር አባሎቹ እውቅና መስጠቱን አስታወቀ

ሰኔ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ብአዴን ህዳር 11 ቀን 35ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ባከበረ ማግስት ፣ የብአዴን ነባር ታጋዮች “እኛ ከህውሃት አንሰን ታይተናል” ሲሉ በስብሰባ መድረኮች ላይ አሰተያየት ከሰጡ በሁዋላ ለ246 ነባር ታጋዮቹ እውቅና ለመስጠት ተገዷል።

67 ተዋጊዮቹ ከአዲስ አበባ የመጡ ሲሆን፣ 200 የሚሆኑት አባሎቹ ደግሞ ከዋግ ህምራ ሰቆጣ የመጡ ናቸው፡፡ ነባር አባሎቹ ላለፉት 25 ዓመታት ተረስተው መክረማቸውን በየመድረኩ በማንሳት ያሰሙት የነበረውን ቅሬታ ኢሳት በተከታታይ በድምጽ ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወቃል። ሽልማቱ የገንዘብ እና መልሶ የማቋቋም ድጋፍን ይጨምራል ተብሎአል።

No comments:

Post a Comment