Monday, June 6, 2016

አርበኞች ግንቦት7 በአውሮፓ የተሳካ የድጋፍ ማሰባሰብ ስራዎችን ሰራ


ግንቦት ፳፱(ሃያ ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ በኖረዌይ ኦስሎ ቅዳሜ ባዘጋጀው ዝግጅት የአርበኞች ግንቦት 7 ሊ/መንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እና ፕ/ር ጌታቸው በጋሻው በእንግድነት ተገኝተዋል።  ከፍተኛ ህዝባዊ የትግል ስሜት በተነጸባረቀበት በዚህ መድረግ፣  ከስዊዲን ፤ ፊንላንድ ፣ ዴንማርክ  እና ከሌሎችም  የአውሮፓ ሃገሮች የመጡ ኢትዮጵያውያን ተካፍለዋል።

በዝግጅቱ ከ800 000 የኖርዌጂያን ክሮነር በላይ  ገቢ መገኘቱንም ለማወቅ ተችሎአል።

በስዊዘርላንድም እንዲሁ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በተገኙበት የተሳካ የገቢ ማሰባሰብ ዝግጅት ተካሂዷል። የሁለቱ ዝግጅቶች ሂደት ፋይል እንደደረሰን ዝርዝር ሪፖርት የምናቀርብ መሆኑን ለመግልጽ እንወዳለን።

No comments:

Post a Comment