Tuesday, April 5, 2016

በሚዲትራኒያን ባህር በኢትዮጵያ እናቶችና ህጻናት ላይ አሰቀቂ አደጋ ደረሰ


መጋቢት ፳፯( ሃያ ሰባት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሃሙስ ፣ መጋቢት 22፣ 2008 ዓም ሌሊት ለአርብ አጥቢያ ከግብጽ ተነስተው ወደ አውሮፓ ለመጉዋዝ ባህር ላይ ባለቡት ሰአት ማእበል መነሳቱን ተከትሎ እስካሁን 9 ኢትዮጵያውያን መሞታቸው የታወቀ ሲሆን፣ ከሙዋቾቹ መካከል አንድ እናት ከሁለት ልጆቹዋ ጋር ይገኙበታል፡፡ 3 ሴቶችና 4 ወንድ ወጣቶት ኢትዮያውያንም በአደጋው አብረው አልቀዋል፡፡
የሁለት ልጆች እናት የሆነችው ግለሰብ፣ ከህጻን ልጆቹዋ ጋር እንዴት አሰቃቂ በሆነ መንገድ እንደሞተች የሚያሳይ ፎቶ ግራፍ ለኢሳት የደረሰ ሲሆን፣ እድሜዋ ወደ 6 አመት የሚጠጋት ህጻንና በ30 ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ መሆኑዋን መገመት የሚቻለው እናት እንዲሁም ወንድ ልጁዋ ሆዳቸው ከላይ እስከ ታች ተቀዶ ፣ ፊታቸው በደም ተሸፍኖ ይታያል፡፡
የሙዋቾቹ የውስጥ አካላት ሙሉ በሙሉ ሳይወጣ እንዳልቀረ መገመት የሚቻል ሲሆን፣ ድርጊቱ ሆስፒታል ውስጥ ይፈጸም ወይም ሌላ ቦታ የታወቀ ነገር የለም፡፡
ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተለውና ከሙዋቾች መካከል የ4ቱ ጉዋደኛና ጎረቤት የሆነ ሰው ፣ የሙዋቾች የቀብር ስነስርዓት እንዲፈጸም ሆስፒታል ተገኝቶ ክትትል በማድረግ ላይ መሆኑን ገልጹዋል፡፡
ጉዋደኞቹን በማጣቱ ከፍተኛ ሀዘን እንደተሰማው የገለጸው ኢትዮጵያዊ፣ አስከሬናቸው ወደ ኢትዮጵያ ሄዶ እንዲቀበር ወይም ክትትል እንዲያደርግ የኢትዮጵያን ኢምባሲ ትብብር ቢጠይቅም ፣ መልስ ሊያገኝ አለመቻሉን በሀዘን ተናግሩዋል፡፡
በጉዳዩ ዙሪያ ካይሮ የሚገኘውን ኢምባሲ ለማናገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

No comments:

Post a Comment