Wednesday, April 6, 2016

በኦሮሚያ ሱሉልታ ተቃውሞ ተካሄደ

ኢሳት (መጋቢት 27 ፥ 2008)

በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ከአራት ወራት በላይ የዘለቀው ተቃውሞ በሳምንቱ መጀመሪያ ሱሉልታ ላይ እንደገና ተከስቷል። ከተለያዩ አካባቢዎች የታሰሩ ነዋሪዎች በጦላይ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ድብደባ እየተፈጸመባቸው መሆኑም ተመልክቷል።
በኦሮሚያ የተቀጣጠለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የተፈጸመውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ የሚከታተሉት የማህበራዊ ሳይንስ ጥናት ባለሙያ አቶ ብርሃኑ ሌንጂሶ ለኢሳት እንደገለጹት 2ሺ 8 መቶ ያህል እስረኞች በጦላይ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ የታሰሩ ሲሆን፣ ድብደባ
እየተፈጸመባቸው ይገኛል። ድብደባውን የሚፈጽሙት የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽንና የኦሮሚያ ማረሚያ ባልደርቦች ሲሆን፣ የህወሃት ሰዎች በቅርብ ሆነው መመሪያ እየሰጡ መሆናቸውም ምንጮቹ ጠቅሶ አስረድቷል።
በዚሁ ጦላ ወታደራዊ ካምፕ በአብዛኛው የታሰሩት የኦሮሞ ተወላጆች ቢሆንም፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ፣ ጋምቤላና ቤኒሻንጉል ክልል የተጋዙ ኢትዮጵያውያንም እንደሚገኙበት ተመልክቷል።
ድብደባውን ወይንም ማሰቃየቱን እንደሚፈጽሙ ሃላፊነት ከተሰጣቸው የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ባልደረቦች አንዳንዶቹ ለምን ወገኖቻቸንን እንደበደባለን የሚል ጥያቄ እያነሱ መሆናቸውም ተመልክቷል።

No comments:

Post a Comment