Thursday, April 28, 2016

ተመድ በቅርቡ በጋምቤላ የተፈጸመውን ግድያና አፈና አወገዘ

ኢሳት (ሚያዚያ 20 ፥ 2008)

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን በቅርቡ በጋምቤላ የተፈጸመውን ግድያና አፈና አወገዘ ፥ በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍንም ጥሪ አቅርቧል። የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ረቡዕ ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ፣ በጋምቤላ የተከሰተ ድንበር ዘለል ግጭት ከ21ሺህ በላይ በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንዳፈናቀለ ገልጿል።

እሳት በቅርቡ እንደዘገበው በኑዌር ዞን በማላዌ፣ በጅካዎና በላሬ ወረዳዎች በሚገኙት ሶስት ወረዳዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መፈናቀላቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጋትሉዊክ ቱት ዋቢ በማድረግ መዘገቡ ይታወሳል።
በሳምንቱ መገባደጃ አርብ በጋምቤላ ክልል በሚኖሩ የኑዌር ጎሳ አባላት ላይ በሙርሌና ዲንቃ ጎሳ ታጣቂዎች ተፈጽሟል በተባለ ጥቃት ከ208 በላይ ኢትዮጵያውያን መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ከ108 የሚበልጡ ህጻናትና ሴቶች ታግተው መወሰዳቸው በአለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ሲዘገብ ቆይቷል።
የኢትዮጵያ መንግስት የሙርሌ ጎሳ አባላት የሆኑና ጥቃቱን ፈጽመዋል በተባሉ ታጣቂዎች ላይ እርምጃን ለመውሰድ ህጻናቱ የታገቱበት አካባቢ ከብቤያለሁ በአጭር ጊዜ አስለቅቃቸዋለሁ ሲል ቢቆይም ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ደቡብ ሱዳን ድረስ ዘልቆ መግባቱና ከበባ መፈጸሙን የሚያመላክት መረጃ አልተገኘም። የደቡብ ሱዳን መንግስትም በጋምቤላ ክልል ከ108 በላይ የተጠለፉትን ህጻናትን ለማስመለስ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር የሚቻለውን እንደሚያደርግ ተናግሮ እንደነበር ይታወሳል።
የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን በጋምቤላ ክልል ጥቃቱ በተፈጸመበት አካባቢና ከደቡብ ሱዳን የመጡ ስደተኞች በሚኖሩበት መጠለያ ካምፕ ሰላምና ጸጥታ ለማስከበር የተሰማሩትን ሃይሎች አመስግኖ፣ እነዚህ ሃይሎች ባይኖሩ ኖሮ ተጨማሪ የአያሌ ዜጎች ህይወት ሊጠፋ ይችል እንደነበር ገልጿል።
በጋምቤላ ክልል ከ272ሺ በላይ ከደቡብ ሱዳን የመጡ ስደተኞች የሚኖሩ ሲሆን አብዛኞቹ ከ2013 የዕርስ በእርስ ግጭት ወቅት ጀምሮ  ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ናቸው። የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ሰላምና መረጋጋት በደቡብ ሱዳን እንዲሰፍን ምኞቱን ገልጾ፣ ስደተኞቹም ወደአገራቸው ደቡብ ሱዳን እንደሚመለሱ፣ እስከዚያው ድረስ ግን አለም አቀፍ ማህበረሰብ ለስደተኞቹ የእርዳታ እጁን

No comments:

Post a Comment