Tuesday, April 19, 2016

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተቃውሞ ገጠማቸው

ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ውይይት ላይ ለመሳተፍ በድንገት ስዊድን የተገኙት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ መረጃው ደርሶአቸው በፍጥነት በተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ገጥሞአቸዋል። ኢትዮጵያውያኑ፣ ደ/ር ቴዎድሮስን፣ ሌባ፣ ገዳይ በማለት ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል።
ወደ ስዊድን እንደሚመጡ አስቀድሞ ሳይነገር በመገኘታቸው ተቃውሞ ለማዘጋጀት አለመቻሉን የሚናገሩት ኢትዮጵያውያን፣ ከያሉበት በስልክ ተደዋውለው በመጠራራት፣ ተቃውሞአቸውን መግለጻቸውን ለኢሳት ተናግረዋል። ዶ/ር አድሃኖም በከፍተኛ የጸጥታ ሰራተኞች ታጅበው ወደ አዳራሹ መግባታቸውን ለኢሳት ከተላው ፊልም መመልከት ይቻላል።

No comments:

Post a Comment