Tuesday, April 12, 2016

አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በ1.1 ብር ሚሊዮን ብር የዋስትና መብት ተፈቀደላቸው

ሚያዚያ ፬( አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአክሰስ ሪልስቴት መስራችና ባለቤት የሆኑት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በአንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ብር ዋስትና የቀረበባቸውን ክስ ውጪ ሆነው መከራከር እንደሚችሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ብያኔወስኗል።

ባለሃብቱን በደረቅ ቼክና በሌሎች የሙስና ወንጀል ክስ ያቀረበባቸው አቃቤ ሕግ የዋስትና መብቱን እንዲነሳ ቢቃወምም ፍርድ ቤቱ ዋስትናውን በመቀበል ውጪ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ሲል ብያኔውን ሰጥቷል።
አቶ ኤርሚያስ አመልጋ የገዥው ፓርቲ አባላትን በማመን በአክሰስ ሪል ስቴት ውስጥ ተፈጥሮ የነበረውን ችግር ለማስተካከል ከሚኖሩበት ከአሜሪካ የተገባላቸውን ዋስትና በማመን መምጣታቸው ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment