Friday, April 8, 2016

የእንግሊዝ የፓርላማ አባላት የአንዳርጋቸውን ጉዳይ ሊ

የእንግሊዝ ፓርላማ የውጪ ጉዳይ ኮሚቴ በውጪ አገራት በእስር ላይ የሚገኙ እንግሊዛዊ ዜግነት ያላቸውን (በኢትዮጵያ የሚገኙትን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ) እስረኞች ጉዳይ በማጥናት መንግስት በውጪ አገራት በሚገኙ እንግሊዛዊያን ላይ የሚፈጸምን የሰብዓዊ መብት ረገጣን  ለማስቀረት የሚያሳየውን ቁርጠኝነት እመዝናለሁ ማለቱ ተሰምቷል፡፡


ትናንት ይፋ የተደረገው ሪፖርት እንደሚያሳየው ከሆነም ብዛት ያላቸው እንግሊዛዊያን በውጪ አገራት ታስረው የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ረገጣዎች ሲፈጸምባቸው መንግስት የሚጠበቅበትን ጫና በማሳረፍ ዜጎቹን ከሚደርስባቸው ጥቃት መከላከል አልቻለም፡፡ባለፈው ዓመት የነሐሴ ወር የወጣን ሪፖርት ኮሚቴው መመልከቱ የተገለጸ ሲሆን በሪፖርቱ መንግስት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለሚፈጽሙ አገራት ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ ለሰብዓዊ መብት መከበር ግድ የማይሰጠው መሆኑን ታዝበዋል ተብሏል፡፡
በፓርላማው የተዋቀረው የውጪ ጉዳይ ኮሚቴ በመንግስት የሰብዓዊ መብት አከባበር ስራ ዙሪያ ጥልቅ ምርመራ እንደሚያደርግ በመግለጽ በውጪ አገራት የሚገኙ እንግሊዛዊያን እየደረሰባቸው የሚገኝን የመብት ጥሰት በዝርዝርና በጥልቀት በመመልከት የሰብዓዊ መብትን ለማስከበር መንግስት የተጓዘውን ርቀት እንደሚቃኝ አውስቷል፡፡
በለንደን የአንዳርጋቸውን ቤተሰቦች በመርዳት ላይ የሚገኘው ሪፕራይቭ የተባለው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እንዳስታወቀው ከሆነም የፓርላማ ቡድኑ በዋናነት የአቶ አንዳጋቸውን ጉዳይ መመርመር ይጀምራል፡፡
አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ ከህግ አግባብ ውጪ መያዛቸውን በመቃወም የተባበሩት መንግስታትና የአውሮፓ ፓርላማ አንዳርጋቸውን ኢትዮጵያ በነጻ እንድትለቅ ሲጠይቁ የእንግሊዝ መንግስት ተመሳሳይ ጥያቄ ሳያቀርብ በመቆየቱ ትችት ሲሰነዘርበት ቆይቷል፡፡ሪፕራይቭ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርትም የዴቪድ ካሜሮን መንግስት ለኢትዮጵያ መንግስት የደህንነት መስሪያ ቤት ዋነኛው ደጋፍ አድራጊ መሆኑን ማጋለጡ አይዘነጋም፡፡
ምንጭ ሪፕራይቭ

No comments:

Post a Comment