Thursday, April 7, 2016

በዱባይ የታሰሩት ኢትዮጵያዊያን ሥጋ ላኪዎችን እስካሁን አልተለቀቁም

መጋቢት ፳፱( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፈው የካቲት ወር ጀምሮ በዱባይ በተካሄደው ዓለምአቀፍ የምግብ ኤግዚብሽን ላይ ለመካፈል በተጓዙበት የተበላሸ ሥጋን አቅርበዋል በሚል ውንጀላ በተባበሩት አረብ ኤሜሬት ፓሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉት የስድስቱን ኢትዮጵያዊያን ሥጋ ላኪዎችን ለማስለቀቅ እንዳልተቻለ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤትና የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር እስረኞቹን ማስፈታት እንዳልቻሉ የተገለፀ ሲሆን የሥጋ ላኪዎች ማኅበር በበኩሉ ለተደጋጋሚ ጊዜያት ተማጽኖውን ቢያቀርብም ችግሩ ከአቅም በላይ መሆኑን አስረድተዋል።
ከአንድ ወር በላይ ሳይፈረድባቸው በእስር የሚማቅቁትን ዜጎች ማስፈታት የተሳናቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለዱባይ አንባሰደር ደብዳቤ መፃፋቸው ታውቋል።
ከወራት በላይ ካለ ፍርድ በእስር የተንገላቱት ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ሲታይ የኢትዮጵያ ኤንባሲና ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች ጨምሮ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ለዜጎች ከለላ የመስጠት አቅማቸው መዳከሙን ያመላክታል ሲሉ ታዛቢዎች ይገልጻሉ።

No comments:

Post a Comment