Tuesday, April 5, 2016

የመን ውስጥ ኢትዮጵያውያን ተገደሉ


መጋቢት ፳፯( ሃያ ሰባት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው አርብ፣ የታጠቁ ሃሎች በአንድ የማሆይ ቴረሳ የድጋፍ ድርጅት ውስጥ በመግባት በፈጸሙት ጥቃት 17 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣ 6ቱ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡
ጥቃቱን ማን እንደፈጸመው በትክክል ባይታወቅም፣ አንድ የኤደን የጸጥታ ሰራተኛ እንዳለው 4 ታጣቂዎች ወደ ገዳሙ በመግባት የጥበቃውን ሰራተኛ ጨምሮ መነኮሳቱንና በውስጥ የነበሩትን ሁሉ ገድለዋቸዋል፡፡ ሙዋቾቹ ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ወደ ሚያስተዳድረው ሆስፒታል መወሰዳቸው ታውቁዋል፡፡
ስለተገደሉት ኢትዮጵያውያን፣ በመንግስት በኩል ምንም የተባለ ነገር የለም፡፡ አይ ኢስ ኤስ እና አልቃይዳ የተባሉት አሸባሪ ቡድኖች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በየመን ሃይላቸውን እያጠናከሩ መምጣታቸውን አሶሽየትድ ፕሬስ ዘግቡዋል፡፡

No comments:

Post a Comment