Friday, April 29, 2016

አቶ ኤርሚያስ አመልጋ የፍርድ ቤት ዋስትና መብታቸው ተገፎ ድጋሚ አዲስ ክስ ተመሰረተባቸው


ሚያዚያ ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአክሰስ ሪልስቴት መስራችና ባለቤት የሆኑት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በፍርድ ቤት በዋስ እንዲወጡ ቢፈረድላቸውም ፓሊስ ተጨማሪ ክስ በማቅረብ የዋስትና መብታቸው ተገፎ ሌላ ክስ መስርቶባቸዋል።
ባለሃብቱ ባለፈው ሳምንት ጉዳያቸውን ውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቢበይንም ፣ፓሊስ ግለሰቡን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። አቶ ኤርሚያስ አመልጋን ለማስለቀቅ ቤተሰቦቻቸውና ጠበቃቸው ያደረጉት ጥረት አለመሳካቱን ከሕግ አግባብ ውጪ ድጋሚ መከሰሳቸውን ተከትሎ እገዳ ተጥሎባቸዋል። ይህም ከፍተኛ ስነ ልቦናዊ ጫና እንደፈጠረባቸው የአቶ ኤርሚያስ ቤተሰቦች በተለይ ለፎርቹን ጋዜጣ ገልፀዋል።

No comments:

Post a Comment