Tuesday, July 14, 2015

ኢህአዴግ ለጅቡቲና ለኤርትራ አፋሮች ስልጠና መስጠት ጀመረ

ሐምሌ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የውስጥ ምንጮች እንደገለጹት ኢህአዴግ የጅቡቲ አፋር እና የኤርትራ አፋር ተቃዋሚዎችን በማሰባሰብ የኤርትራ መንግስት ተቃዋሚ የታጠቁ ሀይሎች በሚል የቀጥታ የመሳሪያ ድጋፍ በማድረግ ስልጠና መስጠት መጀመሩን ምንጮች ገልጸዋል። ሰልጣኞቹ አስመራ ድረስ በመሄድ ስልጣን እንደሚይዙ ተስፋ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በኢትዮጵያ የሚኖሩ የኤርትራ ስደተኞች ወደ ትግሉ እንዲቀላቀሉ ጨና እያሳደረ እንደሚገኝም የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ኢህአዴግ አንዳንድ የአፋር ተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን በማሰባሰብ ፣ በአፋር በኩል ሊሰነዘርበት የሚችለውን ጥቃት ለመከላከል እየሞከረ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment