Monday, July 6, 2015

ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ስለላ ለማድረግ አንድ ሚሊዮን ዶላር ከፍላለች


ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ስለላ ለማድረግ አንድ ሚሊዮን ዶላር ከፍላለች። አፕሪል 18፣ 2012 ከሚላን የ"ሐኪንግ ቲም" ቢሮ የወጣው የክፍያ መጠየቂያ የተላከው ለኢንሳ (የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ)ነው። ክፍያው የተፈጸመለት ሐኪንግ ቲም መቀመጫውን ጣልያን ያደረገ የኢንተርኔት ስለላ መሣሪያዎችና አግልግልቶችን የሚሰጥ ድርጅት ነው። ዜናው አክሎ እንደሚያተተው፣ ከመለስ ዜናዊ ሞት ከስምንት ወራት በኋላ ቢንያም ተወልደ የተባለ ግለሰብ ከመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን ጋራ ግንኙነት ያላቸው ስምንት ዶሜኖችን (የድረ ገጽ ስያሜና አድራሻ፣ የኢሜይል አግልግሎት ወዘተ)አስመዝግቧል ወይም ገዝቷል። ይሁንና እነዚህ ዶሜኖች ድንገት መጥተው ድንገት መሰወራቸው፣ መጀመሪያውኑም የተከፈቱት ለኢንተርኔት ስለላው ሽፋን ለመስጠት እንደሆነ ያስጠረጠራል ተብሏል። አቶ ቢንያም ተወልድ አፕሪል 4፣ 2013 ለሐኪንግ ቲም በጻፈውና ይፋ በወጣው ኤሜል "አንድ ትልቅ ዋጋ ያለው ኢላማችንን ልናገኘው ችልናል" ብሏል። ይህ ትልቅ ዋጋ አለው የተባለውና የኢሜል ስለላና ጠለፋው ሰለባ የሆነው አካል ማንነት ግን አልተገለጠም። አክሎም ከሐኪንግ ቲም የሚያገኘውን አገልግሎት ወይም ቴክኖሎጂ ከፍ ማድረግ እንደሚፈልግ ገልጿል። የሐኪንግ ቲም የኦፐሬሽን ማናጀር በበኩሉ፣ "ትልቅ ዋጋ ያለውን ኢላማችሁን ስላገኛችሁት ደስ ብሎናል" ሲል መልሶለታል። የአንድ ሚልዮን ዶላሩ የክፍያ መጠየቂያ ከተላከ ከዓመት በኋላ በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለው ግንኙነት መቀጠሉ ክፍያው መፈጸሙን አመላካች ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።

No comments:

Post a Comment