Wednesday, July 1, 2015

ለመከላከያ ሰራዊት አባልነት የሚመዘገብ ወጣት መጥፋቱ እየተነገረ ነው

ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመከላከያ ሰራዊት ያወጣው አዲስ የቅጥር ማስታወቂያ ተቀባይነት አለማግኘቱን ከተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። በሰሜን ሸዋ ከሁለት ሳምንት በፊት የወጣውን የቅጥር ማስታወቂያ ተከትሎ ተመዝጋቢ በመጥፋቱ፣ የአካባቢው ባለስልጣናት የሚያደርጉት ጠፍቷቸዋል። በአርባምንጭ ደግሞ የኢህአዴግ ካድሬዎች በመኪና እየዞሩ ወጣቱ ለመከላከያ አባልነት እንዲመዘገብ እየቀሰቀሱ ነው። ይሁን እንጅ ለጥሪው ወጣቱ የሚሰጠው ምላሽ እጅግ አነስተኛ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ።
የመከላከያ ሚኒስትር ከአመት በፊት ላወጣው ማስታወቂያም እንዲሁ የታሰበውን ያክል ወጣት አልተዘመገበም ነበር። መከላከያን እየጣሉ የሚወጡ ወታደሮች መበራከት፣ መንግስት አዳዲስ ምልመላ እንዲያካሂድ ግድ ሳይለው አልቀረም።
መንግስት በዚህ አመት ለመከላከያ ሚኒስቴር ተጨማሪ ባጀት መድቧል። የኢሳት ምንጮች እንደሚሉት በቅርቡ ኣዳዲስ የጦር መሳሪያዎችና ተዋጊ ጄቶች ተገዝተው ወደ አገር ገብተዋል።


No comments:

Post a Comment