Sunday, July 5, 2015

ዓስቸኳይ መልክት ለኢትዮጵያ ሕዝብ፥ በኛ በኩል የትግል ፊሽካው ተነፍቷል

ዓስቸኳይ መልክት ለኢትዮጵያ ሕዝብ፥ በኛ በኩል የትግል ፊሽካው ተነፍቷል፥
በተጀመረው የትግል ጎዳና መግባትና ወያኔን ዓንገት ላንገት ተናንቆ ማስወገዱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳይ ነው ይላል፥
ታጋይ ዘመነ ካሴ ከአርበኞች ግንቦት 7 የጦር ግንባር፥

ይህ ጄግና ሰራዊት በወያኔ ጎጠኛ ቡድን ላይ ታሪክ ሊሰራ ተዘጋቷል፥ ዘንድሮ የእኛ እና የእነሱ ነገር ይለያል እያለ ነው፥

ስለዚህ ውድ ሕይወቱን መስዋዕት ለማድረግ ቆርጦ የወጣን የነጻነት ታጋይ፥ ለሚተቹ፣ እንደ ዓግዳሚ ወንበር የመጣ የሄደውን እያሳለፉ፣ ስንዝር ሳይራመዱ ሲያወሩ ላረጁ፥ ነውራቸውን ለማያቁ ተቃዋሚ ነን ባይ ከንቱ ፖለቲከኞች፥ ወይ ዓትሰሩ ወይ ዓታሰሩምና፥ እባካችሁ ዓፋችሁን ዝጉ ማለት ያስፈልጋል፥

በእልህ ኤርትራ በርሃ ወርዶ፥ ያለውን ሁሉ ጥሎ፥ ብሩህ የድል ቀን ተስፋን በልቡ ሰንቆ፥ እራሱን በቁራጭ ጨርቅ ዓስሮ፣ እንደ እስትንፋሱ የሚያያትን ጠመንጃውን በትካሻው ተሸክሞ፣ ጥይትና ዝናሩን ከጨብጥ ቆሎ ጋር በወገቡ ታጥቆ፥ ቀን በሓሩር፣ ሌሊት በቁር፣ ድንጋይ ትራሱ፣ ዓሸዋ ልብሱ ዓድርጎ፥ ከበርሃ ዓውሬ ጋር ተፋጦ እየኖረ፥ ያን ጨካኝ ጠላት ወያኔን እስከ መጨረሻው እንዳይነሳ ዓርጎ ከሕዝብ ጫንቃ እንዴት እንደሚያንከባለው እያሰላሰለ የሚያንጎራጉረው የቁጭት ቀረርቶ ነው፥

እነዚህ ወጣቶች ከእኔና ከእናንተ የተለየ ኢትዮጵያዊነት ስላላቸው ሳይሆን፣ የባንዲራቸውና የሃገራቸው መዋረድ ዓንገፍግሯቸው፣ የሕዝባቸው መከራና ግፍ ዓስመርሯቸው፣ እንቢ መጠቃትን በዝምታ ዓንቀበልም በማለት፥ የሚከፈለውን ዋጋ ከፍለው ለዓገራቸውና ለሕዝባቸው ነጻነት ለመሞት ሓላፊነት በመውሰድ እራሳቸውን ስላዘጋጁ ብቻ ነው እዚህ ቦታ ላይ እንዲህ የሚንከራተቱት፥

ስለዚህ ውድ ሕይወቱን መስዋዕት ለማድረግ ቆርጦ የወጣን የነጻነት ታጋይ፥ ለሚተቹ፣ እንደ ዓግዳሚ ወንበር የመጣ የሄደውን እያሳለፉ፣ ስንዝር ሳይራመዱ ሲያወሩ ላረጁ፥ ነውራቸውን ለማያቁ ተቃዋሚ ነን ባይ ከንቱ ፖለቲከኞች፥ ወይ ዓትሰሩ ወይ ዓታሰሩምና፥ እባካችሁ ዓፋችሁን ዝጉ ማለት ያስፈልጋል፥
ይህ ጄግና ሰራዊት በወያኔ ጎጠኛ ቡድን ላይ ታሪክ ሊሰራ ተዘጋቷል፥ ዘንድሮ የእኛ እና የእነሱ ነገር ይለያል እያለ ነው፥

No comments:

Post a Comment