Monday, July 13, 2015

አንድ አስገራሚ ታሪክ ከግንባር

የ21 ዓመት ወጣት ነው:: የትህዴን ተዋጊ ወታደር ነው:: በርከት ያሉ የማጥቃት ወታደራዊ ዘመቻዎች ላይ ተሳትፏል:: ….በ2006 እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በየካቲት ወር በአንዱ ዕለት ነው:: የሱ ምድብ ጋንታ ግዳጅ ተሰጥቶት ወደ ትግራይ መሬት ይገባል:: ከጓደኞቹ ጋር በመሆን ከህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ታጣቂዎች ጋር ውጊያ ይገጥማል:: ለሰዓታት በዘለቀው በዚሁ ውጊያ ለአከ የተሰለፈበት የትህዴን ሃይል የማጥቃቱን የበላይነት ይይዛል:: እነ ለአከ በርካታ የህወሀት ታጣቂዎችን እየማረኩ ነው:: …..

….ለአከ በውጊያው መሃል አንድ የህወሀት ታጣቂ መሳሪያውን እንደያዘ ሲሸሽ ተመለከት:: ተከተለው:: ከዚያም መሳሪያውን አስቀምጦ እጅ ወደ ላይ እንዲል አደረገው:: ታጣቂው እንደተባለው አደረገ:: ፊቱን እንዲያዞር አዘዘው:: ፊቱን አዞረ:: ….ለአከ ድንግጥ አለ:: የሚያየውን ማመን አቃተው:: ….ወላጅ አባቱ ናቸው::
እኔ..” አባትህን ስትማርካቸው ምን ተሰማህ?”
ለአከ..” ምን ላድርግ? የዓላማ ጉዳይ ነው::”
ለአከ የማረካቸውን አባቱን ይዞ ወደ ካምፕ ተመለ�ሰ:: አባት ከትህዴን ጋር መቆየት ወይም ወደ ቤተሰብ መመለሥ የሚሉ ምርጫዎች ቀረቡላቸው:: ወደ ቤተሰብ መመለሱን መርጠው ምክር ተሰጥቶአቸው ሄዱ::
እኔ..” አባትህ የማረካቸው ወታደር የእሳቸው ልጅ መሆኑን ሲያውቁ ምን አሉህ?
ለአከ..” ..’በህይወት አለህ? እርማችንን አውጥተን ነበር’..አለኝ”
አባትና ልጅ በተቃራኒ ቡድኖች የተሰለፉበት ታሪክ:: ለአከ “ከዓላማ የሚበልጥ ምንም ነገር የለም” የሚል መልስ ከአፉ አይጠፋም::

No comments:

Post a Comment