Tuesday, December 2, 2014

በአዲስ አበባ 7ቱም የሃይማኖት ተቋማት ለመንግስት የደህንነት ስራ እንደሚሰሩ ታወቀ!

ኢሳት ዜና :-የፌደራል መንግስቱ የ2006 የጸጥታ አጠባበቅ ግምገማ በሚያደርግበት ስብሰባ ላይ እንደተገለጸው በአዲስ አበባ 7ቱም የሃይማኖት ተቋማት ከመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ጋር በጋራ በመቀናጀት የደህንነት ስራ እየሰሩ ነው።

አጠቃላይ ውይይቱን በተመለከተ ለኢሳት የደረሰው ሚስጥራዊ የድምጽ መረጃ እንደሚያስረዳው በአዲስ አበባ በተቋቋመው መዋቅር ውስጥ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች የሚገኙበት ሲሆን፣ መንግስት መኪና፣ ኮምፒዩተር፣ ጽ/ቤትና ሌሎች ቁሳቁሶች ሰጥቷቸው ከመንግስት ጋር በመሆን ጸጥታን ለመከላከል እየሰሩ መሆኑን የአዲስ አበባ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊው በጉባኤው ላይ ተናግረዋ ህገመንግስቱ መንግስትና ሃይማኖት የተለያዩ መሆናቸውን
ቢደነግግም፣ የመንግስት ባለስልጣናት በሚስጢር በሚያደርጉት ስብሰባ የሃይማኖት ተቋማት የመንግስትን የደህንነት ስራ እንደሚሰሩ መግለጻቸውን ከዚህ ቀደም ኢሳት በድምጽ አስድገፎ ማቅረቡ ይታወቃል።

በዚሁ ስብሰባ ላይ የኦሮምያ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ በክልሉ የሚታየውን የዋቄ ፈታ እምነት ለማዳከም እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ተናግረዋል። ባለስልጣኑ ለተሰብሳቢው ሲናገሩ፣ ኦነግ በዋቄ ፈታዎች መጠቀም ይፈልጋል፤ የዋቄ ፈታ ድርጅት ተወካዮችን ስትራቴጂ ለመፈተሽ በስውርም በግልጽም ሰዎችን አሰማርተናል፤ እነሱ በሚያቀርቡት ሪፖርት ላይ ተነስተን እርምጃ እንወስዳለን ብለዋል።

የአዲስ አበባው ተወካይ ከአክራሪነት አንጻር ህዝቡን በአራት ደረጃ በመክፈ ማሰልጠናቸውን የተናገሩ ሲሆን፣ ከ ዲ ወደ ሲ 52 ሰዎች፣ ከቢ ወደ ሲ 4486 ሰዎች ከቢ ወደ ኤ 7980 ሰዎች መለወጣቸውን ተናግረዋል። ሰዎቹ ተለወጡ የተባሉት ቀድሞ ሲከተሉት የነበረውን የሃይማኖት አስተሳሰብ በመተዋቸው ነው።

ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በተሰጡት ስልጠናዎች ላይ ተገንቼ ታዝቢያለሁ ያሉ ሌላ የፌደራል መንግስት ባለስልጣን ደግሞ ከአዲስ አበባ የመጡ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሚጠይቁዋቸው ጥያቄዎች ፈታኞች መሆናቸውን ገልጸው፣ መንግስት በእነሱ ላይ ትኩረት አድርጎ ሊሰራ እንደሚገባ መክረዋል።


No comments:

Post a Comment