Tuesday, December 9, 2014

ቦርድ የወጡ አንዳንድ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሶማሊያ እንዲዘምቱ ጥሪ ቀረበላቸው

ኀዳር ፳፱)  ፳፻፯ ዓ ኢሳት ዜና :-ከዚህ ቀደም ሶማሊያ ውስጥ ዘምተው የነበሩና መከላከያን የአገልግሎት ዘመናቸውን በመጨረስ ወይም በጉዳት የለቀቁ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ መከላከያ ተመልሰው እንዲዘምቱ በደብዳቤ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ጥሪው የደረሳቸው ወታደሮች ጥሪውን ለመቀበል ፈቃደኞች አልሆኑም።

ጥሪ የተደረገላቸው የሰራዊት አባላት “የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለሰላም አስከባሪ ሃይል በሚል ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ በዶላር ቢልክም እግረኛው ሰራዊት የሚከፈለው ገንዘብ እጅግ አነስተኛ በመሆኑ፣ የክፍያ መጠኑ እስካልተሻሻለ ድረስ አንዘምትም” ብለዋል።

ወታደራዊ አዛዦች ከፍተኛ ገንዘብ ሲከፈላቸው ሌላው ወታደር ቤተሰቡን ለማኖር በማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ወታደሮች በመጥቀስ ጥሪ ላቀረበላቸው አካል መልስ መስጠታቸው ታውቋል።


No comments:

Post a Comment