Sunday, December 21, 2014

ጠቅላይ ሚንስትሩ እና ወጣቸው (የአብስራ ዳኛቸው)

           ኢትዮጵያ ከአክሱም ሥርኦ መንግስት አንስቶ በአመራራቸው እና በማስተዳደር ቡቃታቸው እንዲሁም በአነጋገር ለዛቸው የተመሰገኑ መሪዎች ነበሯት። አሁን አሁን ግን ኢትዮጵያ የማስተዳደር ብቃት ያለው መሪ ብቻ ሳይሆን የማሰብና የመናገር ብቃት ጭምር የለው መሪ ካጣች ከሁለት አስርት አመታት በላይ ተቆጠ። አንድ የሀገር ርዕሰ- መስተዳድር ማለት ህዝብን ወክሎ በተለያዩ አለም አቀፍ ቦታዎች ላይ ንግግር ያደርጋል። ታድያ ይህ የሚይደርገው ንግግር ሀገርን ከሀገር ህዝብን ከህዝብ የማያጋጭ መሆን አለበት። ህዝብ መሪያችን መጣ ብሎ ንግግሩን በመናፈቅ የሚጠብቀው ለዛው የሚስብ፣ የተናገረውን የሚፈፅም፣ ግብረ-ገብነት የተሞላ መሆን አለበት።
        ይህን ለማለት ያነሳሳኝ ወያኔ ጠቅላይ ሚንስቴር አድርጎ ያሥቀመጣችው በአንድ ሆስፒታል ምርቃት ላይ ለተሰበሰበው ህዝብ ባሰሙት ንግግር በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ያሉ ኢትዮጵያኖችን ያሳፈረ እና የወያኔ የፕሮፓንዳ ስልት ምን ያህል የወረደ እና ከእውቀት የፀዳ እንደሆነ የታየበት አጋጣሚ ትኩረቴን ስለሳበው እንደ ኢትዮጵያዊነቴ የተሰማኝን ልበል።

          ሲጀመር ጠ/ሚንስቴሩ የሄዱት ሆስፒታል ለመመረቅ ነው ሆኖም ግን እሳቸው ንግግራቸውን ጀምረው እስኪጨርሱ ድረስ ይናገሩ የነበረው በዚህ ሰአት ያለውን የወያኔ ስርአት በመቃወም ከሀገሩ ተሰዶ በተለያዩ አለማት ጩኸቱን በማሰማት ላይ ያለውን ኢትዮጵያዊ በግልፅ በመሳደብ እና በማንጓጠጥ የተሰበሰበውን ህዝብ ቀልብ ለመሳብ እና ትኩረት ለማግኘት ሲሞክሩ ታይተዋል። አንድ ሀገር ያስተዳድራል ተብሎ ከተቀመጠ እና ሀላፊነት ከተጣለበት ሰው የማይጠበቅ የወረደ ንግግር ነበር የተናገሩት።
          ጠቅላይ ሚንስቴሩ ስድብን እና ተራ ፕሮፖጋንዳን መነሻ ያደረጉት በሰሜን አውሮፖ ከሚኖሩት ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ነበር። እሳቸው እንዳሉት ከሆነ በዚይያ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ መኪና ለመግዛት አቅሙ ስለማይፈቅድለት የሰው መኪና እየተደገፈ ፎቶ በመነሳት ባገር ቤት ላሉ ወገኖቹ በጣም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳለ ለማሳየት እና ማስረጃም እንዲሆነው በሶሻል ሚድያው facebook ላይ ይለቃል ብለው ነው። በአሜሪካ የመኪና በጣም ቀላል እንደሆነ እንካን ጠ/ሚንስቴሩ መረጃ ሳይኖራቸው እንደዛ ብለው መናገራቸው ያሳዝናል። ከዛ በላይ ደግሞ በረጅም ጊዜ ክፍያ በቀላሉ ማግኘት እየተቻለ ለምን የሰው መኪና መደገፍ አስፈለገ??? ለነገሩ ጠቅላይ ሚንስቴሩ በወያኔ ፅ/ቤት እየተፈበረከ እንዲናገሩ የሚሰጣቸው ተረተረትን ነው መድረክ ላይ የሚናገሩት። ጠ/ሚንስቴሩ የfacebook ተጠቃሚ መሆናቸው ጥሩ ነው ታድያ ለምን ይሆን ይህ ህዝብ በተለያየ መንገድ ተቃውሞ ሲገልፅላቸው እየሄዱበት ያለው መንገድ ልክ እንዳልሆነ ማወቅ እንዴት ተሳናቸው ወይስ አላየሁም አይኔን ግንባር ያርገው ማለታቸው ነውን?
         ጠቅላይ ሚንስቴሩም ቀጥለው ወደ አረብ ሀገር ጎራ ብለው ሰርተው ለማደር የተሰደዱ እህቶቻችንን "እንደ አበደ ውሻ እየተክለፈልፉ" ብለው ተሳደቡ። መጀመሪያ እንደ ሀገር መሪነታቸው መናገር ያለባቸው ስአትን በጠበቀ መልኩ እና ፀያፍ ከሆኑ ቃላት ተቆጥበው ነበር። ሴት እህቶቻችን በሀገራቸው ተከብረው እንዳይኖሩ ወያኔ ከ20አመት በላይ ምንም አይነት ጥረት ስላላደረገ የሚበሉት አተው ለቤተሰባቸው መድረስ ተስናቸው አይናቸው እያየ ስላላስቻላቸው ተሰደው ከሚያገኙት ቤተሰባቸውን ለማጉረስ መሞከራቸው ለምን ያበደ ውሻ ያስብላቸዋል??? በዛላይ ይህን የድለላ ስራ በበላይነት የሚሰሩት የወያኔ ካድሬዎች መሆናቸው ያስገርማል። ልቦናቸው እያወቀ ወገናችንን ለእንደዚህ አይነት ችግር የሚያበቁት እነሱ ሆነው ዞረው አዛኝ መሳይ ቅቤ አንጓች መሆናቸው ደግሞ በጣም ያሳፍራል
          በአለም ላይ ከሀገር ተሰደን በምንኖር ኢትዮጵያውያን ላይ ስድባቸውን የተያያዙት የወያኔ አሻንጉሊት የአረብ ሀገር እህቶቻችንን ከፍ ዝቅ አድርገው ከሰደቡ በኃላ ወደ አውሮፖ በመሄድ ጀርመን ውስጥ የሚገኙትን ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ጥገኞችን መሳደብ ቀጠሉ ጠ/ሚንስቴሩ እንደተናገሩት ከሆነ ከሀገር ቤት ከየሆነ ሰው ዶሮ ወጥ ለልጆቼ አድርስልኝ እንዳልዋቸው እና ወጥ ይዘው ከኢትዮጵያ ጀርመን እንደተጋዙ ተናግረዋል በዛውም አያይዘው በተሰጣቸው ስልክ ሲደውሉ አልሰራ ብሎዋቸው የጀርመን ጓደኞቻቸው የሀይም ስልክ እንደሆነ ነግረዋቸዋል ሀይም ምን እንደሆነ ሲጠይቁም እስር ቤት እንደሆነ ተነግሮዋቸዋል በእርግጠኝነት ግን ይሄን ሊነግራቸው የሚችለው በጀርመን ያለው የወያኔ ተጠሪ እንጂ ጀርመናዊ እንዳልሆነ እርግጥ ነው። ምክንያቱም ሀይም የሚለው ቃል ጀርመነኛ ሲሆን ትርጉሙም ቤት ወይም መጠለያ ማለት ነው። ጠ/ሚሩ ሀይምን እስር ቤት ቢሉ አይፈረድባቸውም ምክንያቱም ወያኔ በህልማቸውም በእውናቸውም ከእስር ቤት ሌላ ሻል ያለ ነገር እንዳያስቡ ስለሚያደርጋቸው ነው።የሀገሬ ሰው ዶሮ ብታልም ጥሬዋን ነው አለ ጠ/ሚንስቴሩም ቢይልሙ እስር ቤት ነው።

        ወደ ቀድሞ ነገሬ ልመለስ ስልኩን ደጋግመው ቢሞክሩ ስላልሰራላቸው ወጣቸውን ይዘው ሀይም ወዳሉት ቦታ ሄዱ በኃላም ባዮት ነገር እንደተገረሙ በመምሰል የለመዱትን ውሸት መናገር ጀመሩ። ሀይም ውስጥ ዱቄት ነው የሚበሉትም ብለው ተናገሩ። የኢትዮጵያ ጠ/ሚንስቴር ሀይለማርያም በራሳቸው እጅጉን ሊያፍሩ ይገባል ምክንያቱም የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ጠ/ሚንስትር ወጥ አመላላሽ በመሆናቸው ነው።
      ሌላው ይቅርና ይህን ፕሮፓጋንዳን አጥንተው እንዲናገሩ ተፅፎ ሲሰጣቸው ከህሊናቸው ጋር ተስማምተው ይሄ ነገር ተገቢ አይደለም ብለው ማለት ነበረባቸው። ለነገሩ ወያኔ ለሆዱ እንጂ ለህሊናው መች ያድር እና!!! ይሁን እና እሳቸው ህሊናቸውን ሸጥው ይህን ነገር ለማለት ተገደዱ እናም ጀርመን ሀይም ውስጥ ለሚገኝ ኢትዮጵያዊ ወጡን ለማድረስ ሄዱ እንበል ዋናው እና የዘነጉት ጉዳይ ቢኖር ሀይም ውስጥ ተቀምጦ የሚጠብቃቸው ማን እንደሆነ መርሳታቸው ነው። እንደሚታወቀው ሀይም ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወያኔን እና ስርአቱን በመቃወም የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ መልስ እስከሚያገኝ ድረስ በሰላም የሚኖርበት ነው።
       እነዚህ ኢትዮጵያን የወያንኔ ባለስልጣን ያውም ጠ/ሚንስትር የሚኖሩበት ቦታ ድረስ መጥቶላቸው ይቅር እና የወያኔ ባለስልጣናት ያረፋበት ቦታ ድረስ አጠያይቆ በመሄድ በግልፅ ጥላቻቸውን እና ተቋውሟቸውን በመግለፅ የሚታወቁ ናቸው። ታድያ ጠ/ሚንስቴሩ ለማን ይሆን ወጡን ሰጠው የሚሉት??? እንደ ሚታወቀው ወያኔውስጥ የተማረ ሰው የለም ምክያቱም የተማረ ሰው ቢኖር ኖሮ እንደዚህ አይነት ተራ ፕሮፖጋንዳ ለሳቸው በመስጠት እንዲናገሩ ባላደረጉ ነበር። ከምንም በላይ ግን ይቅርታ ምን ማለት እንደሆነ ባስተማሯቸው ነበር።
     እንግዲህ እኔ በታየኝ መልኩ ይችን ብያለሁ

                                                                                                                 ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!
                                                                                                                     የአብስራ ዳኛቸው።

No comments:

Post a Comment