Thursday, December 11, 2014

የኢትዮጵያ መንግሥት ገመና (ተመስገን ደሳለኝ)

ተመስገን ደሳለኝ  (ከዝዋይ እስር ቤት)ነዋሪ “ጄል-አዳብ” (የገሃነም እስር ቤት) እያለ በሚጠራው ማጎሪያ ውስጥ እጅግ በጣም የከፋ ምድራዊ መከራ እንደተቀበለሀዘን በተጫነው ድምፅ ይናገራል፡፡ በሠውነቱ የተለያዩ ክፍሎች ላይ እንደ ፍም ቀልተው የሚታዩት ጠባሳዎቹም ያሳለፈውንሥቃይ አፍ አውጥተው ይመሰክራሉ፡፡ ለአራት ወራት ያህል አንድ ክፍል ውስጥ ለብቻው ተቆልፎበት፤ ሃያ አራት ሠዓታትሙሉ እጆቹ በካቴና ተቀፍድደው፣በቀን ከአምስት ጊዜ በላይ ለምርመራ እየተጠራ ያለዕረፍት ከባድ ስቅየት (ቶርቸር)ሲፈፀምበት ቆይቷል:፡ በመጨረሻም ለአንዲትም ቀን የፍርድ ቤት ደጅ ሳይረግጥ፣ ለኦብነግ አባላት አንድ ፓኬት ሲጋራሲያቀብል እጀ-ከፈንጅ ተይዟል በሚል ክስ የጅጅጋ ዞን ፍርድ ቤት በሞት እንዲቀጣ መወሰኑን እዛው እስር ቤት ሆኖከኢትዮጵያ ሬዲዮ የዜና እወጃ  እና ከቪኦኤ ሶማሊኛ ፕሮግራም ሠምቷል፡፡ከፍርዱ በኋላም በተመሳሳይ ወንጀል ከተከሰሰ አንድ እስረኛ ጋር በካቴና ተጠፍሮ በቀን አንድ እንጀራ ለሁለት ተካፍሎእንዲበላ እንደ ውሻ እየተወረወረለት 60 ቀናትን አሳልፏል፡
፡ መሐሙድ በተለይም በእንቅልፍ ወቅት እርሱ ወይምየሰንሰለት ደባሉ የተገላበጠ እንደሆነ ካቴናው የሚያደርስበትን የመለብለብ ቃጠሎ ሲያስታውስ ዓይኖቹ በእንባ ይሞላሉ፡፡በአሁኑ ወቅት በዝዋይ ማጎሪያ ከባድ ጥበቃ ለሚደረግባቸው ብቻ በተመደበ ‹‹ዘጠነኛ ቤት›› ውስጥ አስራ አንድ ሶማሊኛተናጋሪዎችን ጨምሮ በድምሩ ሰላሳ አራት ሰዎች ጋር ከዛሬ ነገ የግፍ ፍርዱ ተፈጻሚ ሊሆንብኝ ይችላል በሚል ሰቀቀንእየባነነ በስጋት ተጠፍንጎ መኖር ከጀመረ እነሆ ሰባት ዓመት ሊደፍን ሦስት ወራት ብቻ ቀርተውታል፡፡የተዋረደው የፍትሕ ሥርዓት!. . .ርግጥ ነው ይህ በጨረፍታ ያቀረብኩት አሳዛኝ ታሪክ የመሐሙድ የሱፍ ብቻ አይደለም፡፡ ሌሎች ሰባት ‹‹አባሪዎቹ››ስቃዩንም ሆነ የሞት ፍርዱን ይጋሩታል (በነገራችን ላይ በአንድ መዝገብ የተወነጀሉት እነዚህ ስምንት የሞት ፍርደኞች፡-መሐድ ኢብራሂም፣ አረብ ሰዋኔ ዱልባንቲ፣ ሐሰን መሐመድ ዑስማን፣ ሐሰን መሐመድ ዓሊ፣ ሙክታር መሐመድ ዓብዱላሂ፣ከድር ሽኩር ሙሳ እና ካሚል ዓብዱልናስር እንኳን በጋራ መንግሥት ላይ ሊያሴሩ ቀርቶ እርስ በርስም የተዋወቁት እስር ቤትውስጥ ነው፡፡ ከጅጅጋ ወደ ዝዋይ ‹‹ዘጠነኛ ቤት›› ተዘዋውረው በርካታ ዓመታትን ያሳለፉትም በጭካኔው ወደርእንደማይገኝለት የሚነገረው የክልሉ ፕሬዚዳንት አብዲበአደራ እንዲቀመጡ በመተላለፋቸው መሆኑን ነግረውኛል፡፡) እንደ መሐሙድ ሁሉ እነርሱም ፍርድ ቤት ቀርበውአያውቁም፤ ምንም ዓይነት የሰውም ሆነ የሰነድ ማስረጃ አልተቆጠረባቸውም፡፡ እዚህ ጋ የማነሳው አሳዛኝ ገጠመኝከመካከላቸው አንዳቸውም ራዲዮ ስላልነበራቸው የተጣለባቸውን የሞት ፍርድ ውሳኔ የሠሙት፣ ዜናው ከተላለፈ ከበርካታቀናት በኋላ ሬዲዮ ካላቸው እስረኞች መሆኑነው፡፡ ይህ እጅግ አሳፋሪና አስደንጋጭ መንግሥታዊ ውንብድና በደንብ ይብራራ ዘንድ ለተከሳሶቹ ከተሰጣቸው ባለ አንድገፅ የክስ ቻርጅ የሁለቱን ብቻ በአዲስ መስመር እጠቅሳለሁ፡-‹‹በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ አቃቤ ሕግና ፍትሕቢሮ በሶማሌ ክልላዊ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትጅጅጋየዐ/ሕግ/መ/ቁ 90/2000ዝዋይ እስር ቤት ያለውጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከሳሽ፡- ዐ/ሕግተከሳሽ፡- ሐሰን መሐመድ ዑስማን (ሐንን መድቤ)ዕድሜ፡- 21ሥራ፡- ተማሪአድራሻ፡- ጅጅጋ ከተማ፡- 06 ቀበሌወንጀልበ1996ዓ/ም የወጣውን የኤ.ፌ.ዴ.ሪ የመ.መ.ሥ.ሥ.ህ.ቁ. 240(3) እና 251(መ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፣የወንጀል ዝርዝርተከሳሽ ከመስከረም 1999 ዓ.ም. ጀምሮ እራሱን ኦ.ብ.ነ.ግ. እያለ ከሚጠራው ተቃዋሚና አሸባሪ ድርጅት ጋር በራሱፈቃድበዚሁ በጅጅጋ ከተማ ከላይ በተጠቀሰው ዓመተ-ምህረት አባል በመሆን በጫካ በዚሁ አካባቢ ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ጋርበከተማምሆነ በጫካ በመገናኘት በኢኮኖሚ ረገድ የሚያስፈልጋቸውን፡- ጫማ፣ ልብስ የመሳሰለውን እዚያው ድረስ ሄዶ በማቀበልአብሮሲንቀሳቀስ በመቆየቱ ተከሶ ቀርቧል፡፡››ሁለተኛው የክስ ቻርጅ ደግሞ እንዲህ ይነበባል፡-‹‹በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ አቃቤ ሕግና ፍትሕ ቢሮበሶ/ክ/መ/ ጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትጅጅጋየዐ/ሕ/መ/ቁ 90/2000ከሳሽ፡- ዐ/ሕግተከሳሽ፡- መሐድ ሼክ ኢብራሂምዕድሜ፡- 28ሥራ፡- የለውምአድራሻ፡- ጅጅጋ ከተማ፡- ቀበሌ 051ኛ ክስወንጀሉበ1996 ዓ/ም የወጣውን የኤ.ፌ.ዴ.ሪ የመ/መ/ህ/ ቁ. 241 እና 251(መ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፣የወንጀሉ ዝርዝርተከሳሹ በ1998 ዓ.ም. ወራትና ቀኑ በውል ካልታወቀ ጊዜ ጀምሮ እራሱን ኦ.ብ.ነ.ግ. እያለ ከሚጠራው ተቃዋሚ የፖለቲካድርጅትና አሸባሪ ጋር በራሱ ፈቃድ አባል በመሆን ከዚህ ሕገ-መንግሥቱን ከሚፃረር ድርጅት በቀጥታ ፌዴሬሽኑእንዲከፋፈል፣ ክልሉንየመገንጠል ዓላማ ለማሳካት ይህንኑ ድርጅት ከዚሁ በጅጅጋ ከተማ ለጊዜው ካልተያዘ ግብረ-አበሩ ጋር በመሆን ይህንኑአሸባሪ ድርጅትበሚያስፈልገው ማቴሪያል ሁሉ፡- ጫማ፣ የፖሊስ የደንብ ልብስ፣ መድሃኒት. . . የመሳሰለውን በማቀበሉ፡፡2ኛ ክስወንጀሉበ1996ዓ/ም የወጣውን የኤ.ፌ.ዴ.ሪ የመ/መ/ህ/ ቁ. 36 (ለ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፣የወንጀሉ ዝርዝርተከሳሹ ከ1996 ዓ.ም. ጀምሮ የተለያዩ መ/ቤቶች ማለትም፡- የክልሉ ት/ቢሮን፣ የቀብሪ-ደሐር ት/ቢሮን፣ እንዲሁም የMSFእና የተለያዩ መሥሪያ ቤቶችን እና የትምህርት ተቋማትን ማህተም በማስመሰል አትሞ እና የኃላፊዎችን ፊርማ ዓይነትአስመስሎበማስፈር ሐሰተኛ ሰነድ አዘጋጅቶ በመገኘቱ ተከሶ ቀርቧል፡፡››(ሁሉም የክስ ቻርጆች ማኅተም እና አንጋው አፈወርቅ ምንተስኖት የተባለ የክልሉ ዐቃቤ ሕግ ፊርማ አላቸው)እነሆም ያለአንድ ምስክር፣ ያለምንም የሰነድ ማሰረጃ፣ አንድም ቀን ችሎት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃል ሳይጠየቁ እናሳይከራከሩ (ያውም የዞን ፍርድ ቤት) በነዚህ በስም በጠቀስኳቸው በስምንቱ ኢትዮጵያውን ላይ የሞት ቅጣትን የመሰለየመጨረሻውሳኔ እንደቀልድ አስተላልፎባቸዋል፡፡ (በነገራችን ላይ ሌሎች 13 የኢትዮጵያ-ሶማሌ ተወላጆችም በተመሳሳይ የሐሰትውንጀላ የዕድሜልክ እስር ተፈርዶባቸው ዝዋይ ይገኛሉ፡፡ የሚገርመው ጉዳይ ደግሞ ም ቢሆኑ መጀመሪያ ተጠርጥረው በተያዙበት ወንጀልአይደለምየተጠየቁት፡፡ ጉዳዩ ጭራሽኑ በምርመራም ወቅት አልተነሳም) መቼም በዚህ መልኩ በተቀናበረ የውሸት ክስ ከ20-27 ዓመት የሚገኙወጣቶችን በሲኦላዊ እሳተ-ነበልባል ስቅየት ውስጥ እንዲያልፉ ከማድረግም በዘለለ፣ ብሩህ ቀናቸውን አጨልሞ ላይመለሱወደመቃብርየሚሸኝ ቅጣት ሲጣል ከመመልከት የበለጠ የትኛውንም ዜጋ የሕሊና ስቃይ ውስጥ ከትቶ፣ አንገት አስደፍቶ፣ በቁጣ ቀስቅሶወደአደባባይ የሚያወጣ ገፊ-ምክንያት አለ ብዬ አላምንም፡፡
ማነው ተጠያቂው?በእነዚህ ንፁሃን ኢትዮጵያውያን ላይ ‹በጄል-አደብ› የደረሰባቸው በነውረኝነት የታጀለ ኢ-ፍትሐዊ ፍርድ እና ስቅየት፣የሥርዓቱን እውነተኛ ማንነት ገሃድ የሚያወጣ ተጨባጭ ተግባር መሆኑ ባይካድም፡ ይህንን አረሜናዊ ድርጊት በፊት-አውራሪነትየመሩት፡- ኮሎኔል ሞኒ መንገሻ በጊዜው የክልሉ የፀረ-ሽብር ግብረ-ኃይል ዋና ኃላፊ የነበረ አሁን ወደአዲስ አበባ ተቀይሮ‹ሕገ-ወጥየሠው ዝውውር ወንጀል መከላከል› ኃላፊ፣ ቢኒያም የተባለ የክልሉ የደህንነት ኃላፊ፣ ሻለቃ ዘገየ በክልሉ የፌዴራል ፖሊስኃላፊ፣ወልደአራዌ የክልሉ ፖሊስ ም/ኮሚሽነር፤ እንዲሁም ሻለቃ ወንድሜ፣ ሻለቃ በለጠ እና ታሰረ የተባሉ ኃላፊነታቸውንለይተውየማያስታውሷቸው ግለሰቦች መሆናቸውን ግፉአኖቹ በተሰበረ ልብ፣ ምሬት በሞላው ድምፅ፣ ተስፋ በቆረጠ ስሜትሲተርኩልኝ ዓይኖቼላይ የተቋጠረው የእንባ ከረጢት ገንፍሎ እንዳይፈስ ብርቱ ትግል ማድረጌን አልሸሽግም፡፡የሆነው ሆኖ እነዚህ የሥርዓቱ ሹማምንት የፍርድ ቤት ደጅ ሳይረግጡ፣ የሞት ቅጣት እንዲተላለፍባቸው ባደረጓቸውምስኪኖች ላይ የማሰቃያ ጥበቦቻቸውን በሙሉ ከሞከሩባቸው በኋላ፡- ‹‹ሞት እንፈርድባችኋለን!!›› እያሉ ያስፈራሯቸውናይዝቱባቸውነበር፤ እነርሱም፡- ‹‹እናንተ ፍርድ ቤት ናችሁ እንዴ?›› ብለው በግርምትና ባለማመን ሲጠይቋቸው፣ ማናአህሎኝነትያሳበጣቸው የፀጥታኃላፊዎች እንዲህ በማለት አስረግጠው መልስ መስጠታቸውን ሰምቻለሁ፡-‹‹አዎን! ፍርድ ቤት ማለት እኛ ነን!!››በርግጥ ከዚህ ሁሉ መከራ በኋላ የተላለፈባቸው ውሳኔ፣ ያውም በሞት እንዲቀጡ የሚል መሆኑን ስናስተውል የዛቻውንመነሾ መረዳቱ አዳጋች አይሆንብንም፡፡ በአናቱም በምርመራ ወቅት ዕድል ፊቷን ያዞረችበትን ተጠርጣሪ እዛው እስረኛ ፊትበሽጉጥግንባሩን በርቅሰው እንደ መናኛ ነገር ሜዳ ላይ ይዘረጉት እንደነበረ የዓይን እማኞች ይመሰክራሉ፡፡በጥቅሉ ይህ ሁነት በሀገሪቱ አለቅጥ የተንሰራፋውን የፍትሕ እጦት፣ የሠብአዊ መብት ጥሰት፣ ዳኞች ከሕግ ይልቅ ከቤተ-መንግሥት በሚላክላቸው የፍርድ ውሳኔ ንፁሃኑን ለምድራዊ ስቃይ ከመዳረግም አልፈው ተርፈው በጭካኔሕይወታቸውንምእንደሚነጠቁ በቂ ማስረጃ ይመስለኛል፡፡
‹‹ጄል-አዳብ››የክልሉ ኗሪዎች ‹‹ጄል-አዳብ›› (የገሃነም እስር ቤት) እያሉ የሚጠሩት የጅጅጋው ማሰቃያ ቤት ክፍሎች የተሠሩት አራትመቶታሳሪዎችን እንዲይዙ ታስቦ ቢሆንም፣ አብዛኛውን ጊዜ ከአራት ሺህ በላይ ታሳሪዎች እንደሚታጎሩበት አረጋግጫለሁ፡፡ይህም አንድሰው ከአንድ ሰዓት በላይ በእንቅልፍ ማሳለፍ እንዳይችል አድርጎታል፡፡ ምክንያቱም ቦታውን ለተረኛው የመልቀቅ ግዴታአለበትና፡፡ምናልባት እንቅልፍ ቢጥለው እንኳ ተረኞቹ ቀስቅሰው (ጎትተው) ያስነሱታል፡፡ከ‹‹ጄል-አዳብ›› በሕይወት ተርፎ የሚወጣ ሰው ዕድለኛ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ በዚህ ቦታ ከቤተሰብ ጋር መገናኘት ጭራሽአይሞከርም፡፡ ማሰቡ እንኳ እንደ ቅንጦት ነው የሚታየው፡፡ በእስር ቤቱ አጥር ሦስት መቶ ሜትር ክልል ርቀት ዙርያ ውስጥመገኘትምለከባድ ስቃይ (አንዳንዴም ለሞት ቅጣት) ይዳርጋል፡፡ በሃያ አራት ሰዓት አንዴ፣ አንድ እንጀራ ለሦስት እየተቃመሱለአምስት ዓመትበዛ እስር ቤት ያሳለፈ ምስኪን አጋጥሞኛል፡፡ ይህ ወጣት በ2004ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ ሦስት ዓይነት ተላላፊ በሽታ(ተቅማጥ፣ሰውነትን የሚያሳክክና ጉሮሮን አሳብጦ ለአዕምሮ መቃወስ የሚዳርግ) ተከስቶ በቀን እስከ አስራ አራት ሰው ድረስ ይሞትእንደነበርያስታውሳል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ሕክምና ብሎ ነገር አልነበረም፡፡ እንዲያውም በግልባጩ የክልሉ አስተዳዳሪዎችጭካኔያቸውን (ኢ-ሠብአዊነታቸውን) ወለል አድርገው የሚያሳብቁ ድርጊቶች መፈፀማቸውን አላቋረጡም፡፡ ለማሳያ ያህልም እስረኛው ከሌሊቱስድስትሰዓት ላይ በአንድ ድምፅ እንዲህ የሚል መፈክር እንዲያሰማ መገደዱን እዚህ ጋ መጠቀስ ይቻላል፡-‹‹መለስ ዜናዊ ሐኖላዶ!›› (መለስ ዜናዊ ለዘላለም ይኑር!)‹‹አብዲ ሑመድ ዑመር ሐኖላዶ!››‹‹ኢትዮጵያ ሐኖላዶ!››ኦብነግ ሐዳኦዶ!›› (ኦብነግ ይውደም!)ሌላው አስገራሚ ጉዳይ ቤተሰብ ታሳሪ ልጁ በሕይወት ይኑር ይሙት የሚያውቀውከማጎሪያው በስንት ጊዜ አንዴ የሚፈታሰው ሲገኝ ብቻ የመሆኑ እውነታ ነው፡፡ እናም ድንገት በአንዲት ‹ዕድለኛ› ቀን አንድ ታሳሪ ከ‹‹ጄል-አዳብ›› የተለቀቀእንደሆነ ወሬውከመቅጽበት ይዛመትና ለሳምንታት አሊያም ለወራት የእስረኛው ቤት በእንግዶች እስከ አፍ-ገደፉ ጢም ብሎ ይውላል፡፡የተለመደነውና እሱም ያለመታከት የቀረበለትን ጥያቄ በሚከተለው መልኩ ሲመልስ ይከርማል፡-‹‹ኦ!… እገሌ ከሞተ እኮ ሁለት ዓመት አለፈው›› ፤ “እገሌማ ሲያሳዝን! ካረፈ ገና አንድ ወሩ ነው”፤ “ኦ! እገሌ ለወደፊቱእግዜር ይጠብቀው እንጂ እስካሁን በሕይወት ይገኛል…” ወዘተ ወዘተ. . .

No comments:

Post a Comment