Wednesday, December 17, 2014

የአርበኞችና ግንቦት ሰባት ዲሞክራሲያዊ ግንባር በአስመራ ሊመሰረት ነው::የግንቦት ሰባት አመራር አባላት አስመራ ገቡ ::

ከአስመራ ከተማ የሚገኙ ምንጮቼ በስልክ እንዳስታወኩኝ ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ የግንቦት ሰባት አመራር አባላት የሆኑት አቶ ነእመን ዘለቀ:የአቶ አንዳርጋቸው ወንድም አቶ ብዙአየሁ ጽጌ አቶ አበበ ቦጋለ እና ሌሎች የኢሳት ሪፖርተሮችን አስከትለው አስመራ የገቡ ሲሆን የአርበኞች ግንባር አመራሮች ወደ አስመራ የሚልኩትን ሰው መርጠው ባለመጨረሳቸው እንደዘገዩ ሲጠቆም እስከ እሁድ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል::ዶክተር ብርሃኑ ነጋ መግባታቸውን ለማረጋገጥ ቢሞከርም ሆተሎች ጥብቅ የጸጥታ ክትትል ስለሚደረግባቸው መረጃዎች ለጊዜው እንዲዘገዩ ተደርጓል::


በአስመራ የተለያየ ሆተል ማረፊያ የተዘጋጀላቸው የግንቦት ሰባት አመራሮች የአርበኞች ግንባር አመራሮች እንደገቡ በመጭው አዲስ አመር ጥር መጀመሪያ የውህደት መስራች ጉባያቸውን በማድረግ የአርበኞችና ግንቦት ሰባት ዲሞክራሲያዊ ግንባር ይመሰርታሉ ተብሎ ሲጠበቅ ውህደቱን የአርበኞች ግንቦት ሰባት ደምህት እና ሻእቢያ ሰራዊቶች ሊያጅቡት ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል ሲሉ ምንጮቹ ከአስመራ ገልጸዋል::

እንደ ደምሕት እና ኦነግ እንዲሁም የጋምቤላ ቤንሻንጉል እና አፋር ነጻ አውጪዎች በውህደቱ እንዳይሳተፉ ተደርጓል ያሉት የአስመራ ምንጮች ሻእቢያ የጎሳ ድርጅቶችን ለአላማው ስለሚተቀምባቸው ከአንድነት ሃይሎች ጋር እንዲዋሃዱ አይፈሊግም ሲሉ ተናግረዋል::(በዚህ ጉዳይ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ምንጮቹ አሁን እንዳይጻፍ ጠይቀዋል::)

የአይሮፕላን ወጪያቸውን ሸፍነው አስነራ የደረሱት ነጻ አውጪዎች በሻእቢያ አስመራ ከተማ ውስጥ ሙሉ ወጪያቸው ሲሸፈን የመብራት አገልግሎት እንዳይቋረጥባቸው ጄኔራተር በመትከል እና እንዲሁም የደህንነት እና የጸጥታ ጥበቃ በማድረግ ላይ እንደሆነ ምንጮቹ ሲናገሩ በግንባር ያገኟቸው የግንቦት ሰባት ሰዎች ለጊዜው ዝርዝር ምረጃ ሊሰጡ ፈቃደኞች እንዳልሆኑ ገልጸዋል::

በውህደቱ ዙሪያ በአርማጮ በረሃ ያሉትን የአማራ ፎርስ ሰራዊት አመራሮችን አነጋግሬቸው እንደመለሱልኝ ከሆነ ክታሰሩ አባሎቶቻችን ውጪ በአስመራ ያለንን ሃይል ያስወጣን እና ከሻእቢያ ጋር ያለውን ግንኙነት ዘግተናል ሲሉ የገለጹ ሲሆን ካሁን በፊት ባወጡት መግለጫ ከአስመራ መንግስት ጋር ሆኖ ዪትዮጵያን ህዝብ ነጻነት ማሰብ ስህተት መፍጠር ነው ሲሉ ገልጸው ነበር::በአስመራ በኩል የተዘጋጁትን ነጻ አውጪዎች የተሳካ ቀሪ ዘመን እየተመኘው ቀሪ ዝርዝር ዘገባ ይዤ ለመመለስ ቃል እገባለሁ:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

No comments:

Post a Comment