Thursday, December 11, 2014

የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ምሁራን ወያኔን እና ህጉን አብጠለጠሉት:

ሚዲያው በመንግሥት ሥር መውደቁ ለሰብአዊ መብቶች አለመከበር ምክንያት ሆኗል::

ዛሬ የሰብአዊ መብቶች ቀን ነው፡፡ የዩኒቨርሲቲው የሰብአዊ መብቶች ጥናት ክፍልም ቀኑን አስመልክቶ አንጋፋ የዩኒቨርሲቲውን ምሁራን ጋብዞ ውይይት በማድረገት ላይ ይገኛል፡፡ እስካኹን ከሥነሰብ (አንትሮፖሎጂ)፣ ከጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን ትምህርት ቤት፣ ከፖለቲካል ሳይንስና ዓለም ዐቀፍ ግንኙነት ክፍል እንዲኹም ከሕግና አስተዳደር ኮሌጅ የተውጣጡ ምሁራን ወረቀቶችን አቅርበዋል፡፡

ከጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን ትምህርት ቤት የመጡት ምሁር ሚዲያው በመንግሥት ፍጹም ቁጥጥር ሥር መውደቁ ለሰብአዊ መብቶች አለመከበር ምክንያትና ምልክት እንደኾነ አመልክተዋል፤ ከሕግና አስተዳደር ኮሌጅ የመጡት ምሁር በበኩላቸው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣንን ሠራተኞች የሚመለከተውን ዋስትና ከልካይ ሕግ፣ የፀረ ሽብር ሕጉን፣ የሲቪክ ማኅበራትን ዐዋጅ ሰብአዊ መብትና ሕግ የተጣሉባቸው መኾናቸውን አሥምረውበታል፡፡

ከፖለቲካል ሳይንስ ክፍል የተገኙት ምሁር ዓለም ዐቀፉ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ የሚመለከተው ግለሰቦችን ቢኾንም መብቶቹን እንዲጠብቁ አደራ የሰጠው ግን ለመንግሥታት መኾኑ በራሱ ድክመት እንደኾነ አመልክተዋል፡፡ የእኔ መብት አደራ መሰጠት ያለበት ለእኔ እንጂ ለማንም አይደለም፡፡ በልማታዊ ዐይን ካየነው ስብሰባው ሊበራሊዝምንና ሊበራል አስተሳሰቦችን የሚያስፋፋ ነው፡፡


No comments:

Post a Comment