Friday, December 26, 2014

ገዥው ፓርቲ ባህርዳር ላይ የተደረገውን ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ የሚቃወም የድጋፍ ሰልፍ ሊጠራ ነው

በሰልፉ የማይገኝ ቅጣት ይጠብቀዋል ተብሏል
ገዥው ፓርቲ በአማራ ክልል አስተዳደር ባህር ዳር ከተማ የቤተ ክርስቲያን ንብረት የሆነውን የታቦት ማደሪያ ለመንገድና ለጥቃቅንና አነስተኛ ሱቆች መስሪያ እንዲነጠቅ ማዘዙን ተከትሎ በባህር ዳር ቀደም ሲል የተካሄደውን ህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ የሚቃወም የድጋፍ ሰልፍ ሊጠራ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡
መንግስት ታህሳስ 9/2007 ዓ.ም የተደረገውን ህዝባዊ ተቃውሞ የ‹‹ፀረ ሰላም ኃይሎች እጅ እንዳለበት›› በመግለጽ ‹‹ህገ-ወጥ ሰልፍ›› ማለቱ የሚታወስ ሲሆን ባህር ዳር ከተማ የሚገኙት የቀበሌ ካድሬዎች የተደረገውን ህዝባዊ ተቃውሞ የሚቃወም የድጋፍ ሰልፍ ለማድረግ እያስተባበሩ እንደሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ የቀበሌ ካድሬዎች በየ ቤቱ እየሄዱ የነዋሪዎችን ስም በመመዝገብ በሰልፉ የማይሳተፍ ሰው ቅጣት እንደሚጠብቀው እያስጠነቀቁ እንደሆነ ተገልጾአል፡፡ የድጋፍ ሰልፉ ታህሳስ 21 ወይንም 22 ቀን 2007 ዓ.ም ይደረጋል ተብሎ ይታሰባል፡፡



No comments:

Post a Comment