Monday, December 22, 2014

ከመከላከያ ሰራዊት እንዲባረሩ የታሰቡ ከፍተኛ ባለማእረግ መኮንኖች ለስርአቱ ደህንነት ሲባል በቦታቸው እንዲቆዩ መደረጉ ታወቀ::

በከፍተኛ የመከላከያ ሰራዊት አመራር ውስጥ በከፍተኛ ሃላፊነት ሲሰራ የነበረው ሌተናል ጄነራል አበባው ታደሰ ባለፈው አመት ከቦታው መባረሩ ተከትሎ መባረር አለባቸው ተብለው ውስጥ ለውስጥ የተጨረሰላቸው በርካታ ከፍተኛ ባለማእረግ መኮንኖች ቢኖሩም፤ ከኋላ ሊነሳ የሚችለውን ችግር ግምት ውስጥ በማስገባት በተደረገው ግምገማ ላይ በማስጠንቀቅያ ብቻ እንዲታለፉ መደረጉን ታውቋል::

መባረር አለባቸው ተብለው ከተቀመጡት ከፍተኛ መኮነኖች አብዛኛዎቹ የሌተናል ኮረኔል ማእረግ ያላቸው እንደሆኑ የገለፀው መረጃው የጄኔራል አበባው ተከታዮች ስለሆኑና እንቅፋት ስለሚፈጥሩብን ተብለው እንዲባረሩ የተወሰነባቸው ቢሆንም፤ በመጪው ምርጫ ታሳቢ በማድረግ በህዝቡ መሃል ገብተው ኢህአዴግን ለመጣል ሊያነሳሱ ስለሚችሉ ግምገማ በማድረግ በማሰጠንቀቂያ እንዲታለፉ መደረጋቸውን መረጃዎች አምልክተዋል::መረጃዉም አያይዞ እንደጠቀሰው ክምርጫ መረጋጋት በኋላ በርካታ መኮንኖች ሊባረሩ ይችላሉ::


No comments:

Post a Comment