Wednesday, December 17, 2014

የቀድሞ ኢቲቪ የአሁኑ ኢብኮ ትርምስ ውስጥ ነው።

የተመልካች ድርቅ የመታው ኢቲቪ ጭንቅ ውስጥ እንዳለ ማነው የሚረዳው? ጭንቀቱ ሲጀማምረው መጀሪያ ስሙን ቀየረ።መች ችግሩ ከስሙ ሆነና!በማስከተል ሎጎውን ቀየረው።የቢቢሲን ኮፒ አድርጎ አሳየን።ይህንንም ለአንድ ወር ሳይገለገልበት አሁን በሚጠቀምበት በአረንጏዴ ቀየረው።መደበኛ ዜና መግቢያው ከአፍሪካ ዋንጫ መግቢያ ተመሳሳይ ነው።እንደውም ስፖርት የሚጀምር ይመስላል።ይህም አንድ ወር መቆየቱ እንጃ! በዚህም ስላረካ እባካቹ ተመልካቾች ሎጎ ምረጡልኝ በስምንት መቶ ምናምን ቁጥር ኤስኤምኤስ አድርጉ ይለናል።ታየኝ የሱን ሎጎ ለመምረጠ ቴክስት ስናረግ። የዚህ ጉደኛ ድርጅት መች በዚህ አበቃ አብረው ከሚሰሩት ጋርም እየተባላ ይገኛል።ተወዳጅ የሆነው ባላገሩ አይዶል ባለፈው ቅዳሜ ሳይተላለፍ ቀርቷል።አንደሰማሁት ከሆነ ከአብርሃም ወልዴ ጋር ውዝግብ ውስጥ ናቸው።ከዚህም በተጨማሪ ከዳና ድራማ አዘጋጆች ጋር አለመግባባት ተከስቷል። ለውዝግቡ ዋና ምክንያት ዳና ድራማ በሚተላለፍበት ቀን እና ሰዓት ከቀጣዩ ወር ጀምሮ ሌላ አዲስ ድራማ መተላለፍ እንደሚጀምር ከተነገረ በኃላ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል።ለመሆኑ የዚህ ሁሉ ትርምስ ምክንያት ኢቲቪ ተመልካች ስላጣ ይሆን?አይደለም ቀድሞስ ተመልካች ነበረው እንዴ? ትልቅ እራስምታት የሆነበት ኢሳት ከያንዳዱ ቤት የካድሬዎችን ጨምሮ ዘልቆ መግባቱ ነው።በተለይ የሚያቀርበው ዜና ታአማኒ ከመሆኑ በተጨማሪ በመዝናኛው ፕሮግራም በታማኝ ሾ ታዋቂ አርቲስቶች በእንግድነት መጋበዛቸው ኢቲቪ ከነመፈጠሩም እንዲዘነጋ ኢሳት የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል።በርግጥም ኢቢኤስም ቢሆን ኢቲቪ ተመልካች አልባ እንዲሆን መጠነኛ ተፅኖ ፈጥሯል።እናም እንሆ የኢቲቪ ትርምስ ይቀጥላል።ሳይወድ በግድ ለነፃ ሚዲያዎች ቢሮውን ክፍት የሚያረግበት ቀን እሩቅ አይደለም።
ኢትዮጵያ ለዘልዓለም ትኑር!!!!!!ታሜ የገብርዬ ልጅ


No comments:

Post a Comment