Thursday, December 4, 2014

ከ5 ሚሊዮን የማያንሰው ዐማራ ዬት ደረሰ?

የትግሬ-ወያኔ ለ17 ዓመታት በሽፍትነት፣ ለ23 ዓመታት ደግሞ በገዢነት ተፈናጦ በዐማራ ሕዝብ ባደረሰው የዘር ማጽዳት እና የዘር ማጥፋት ዘመቻ ምን ያህል ንፁሃን ዐማሮች እንደተጨፈጨፉ የተለያዩ አስተያዬቶች ሲደመጡ ቆይተዋል። ሞረሽ ወገኔ ባደረገው ዝርዝር የሕዝብ ብዛት ቆጠራ ትንተና መሠረት ከ1983ዓ.ም. ወዲህ ደብዛቸው ከምድረ-ገፅ እንዲጠፉ የተደረጉት ዐማሮች ብዛት ከ5 ሚሊዮን እንደማያንስ ይጠቁማል። ይህ ምንን ያመለክታል? ከጥናቱ ውጤት የሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ጎልተው ይወጣሉ።



በኢትዮጵያ የመጀመሪያው አገር አቀፍ ብሔራዊ የሕዝብ ቆጠራ የተካሄደው በ1976 ዓ.ም. ነበር። በወቅቱ ኤርትራን እና የአሰብ አስተዳደርን ጨምሮ ጠቅላላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት 42,616,876 ይሆናል። በወቅቱ በሕዝብ ብዛት አንደኛ የነበረው የኦሮሞ ነገድ ብዛቱም 12,387,664 ሲሆን፤ እንዲሁም ዐማራ በሁለተኛ ደረጃ12,055,250 ያህል ተወላጆች ነበሯቸው። ስለሆነም በወቅቱ በሁለቱ ነገዶች ተወላጆች ብዛት መካከል የነበረው የቁጥር ልዩነት 332,414 ይሆናል ማለት ነው። የመጀመሪያው የሕዝብ ቆጠራ ከተደረገ ከ23 ዓመታት በኋላ፣ ማለትም በ1999 ዓ.ም. በተደረገው ሦሥተኛው የሕዝብ ቆጠራ ውጤት መሠረት ዐማራው ቁጥሩ በአዝጋሚ ሁኔታ ወደ 19,867,817 ሲጨምር የኦሮሞዎቹ ብዛት ግን ከእጥፍ በላይ አድጎ ወደ25,488,344 ደርሷል። ስለዚህ በኦሮሞ እና ዐማራ ተወላጆች ብዛት መካከል ያለው የቁጥር ልዩነት 5,620,527 አይበልጥም። በመሆኑም ከ5ሚሊዮን የማያንሰውን ዐማራ ዬት እንዳደረሱት የሚያውቁት የትግሬ-ወያኔዎች እና ሎሌዎቻቸው ናቸው።

ባለፉት 23 ዓመታት ከ4,751,333 በላይ የዐማራ ነገድ ተወላጅ የጠፋው ወያኔ ገና የትጥቅ ትግል ሲጀምር «የትግራይ ሕዝብ ደመኛ ጠላት ዐማራ ነው፤» « ዐማራን፣ የአማርኛ ቋንቋን እና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ማጥፋት አለብን!» ብለው የተሰለፉ በመሆናቸው የዐማራውን ነገድ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በመግደላቸው ነው። በግልፅ እንደሚታወቀው ወያኔ የዐማራውን ነገድ በሚከተሉት ሥልቶች አጥፍቷል። እያጠፋም ነው፥

በተለያዩ ሰበቦች በጅምላ በመግደል፦ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በጠለምት፣ በሠቲት፣ በአርማጭሆ፣ በራያ ሕዝብ ላይ የፈፀሙት የግፍ ግድያ፣

ለዐማራው ነገድ ቁጥር መቀነስ ዋና እና ተያያዥ ምክንያቶች ናቸው። ስለሆነም ያለምንም ማወላወል የዐማራው ነገድ በትግሬ-ወያኔ በተከፈተበት የማያባራ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ዘመቻ ሰለባ መሆኑን ትውልዱ ሊገነዘበው ይገባል።

በተለይ ለዐማራው ነገድ ተወላጆች እና ለሃቀኛ ኢትዮጵያውያን የቀረበ ጥሪ፦

ይህን መረጃ በማባዛት ለዓለም ሕዝብ ባሉት የመገናኛ መሣሪያዎች በመጠቀም በማሰራጨት፣ ሆን ተብሎ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለተፈጸመበት የዐማራ ነገድ ድምፅ ልንሆን ይገባል። ለተበደሉ እና የመኖር ሰብአዊ መብት ለተነፈጋቸው ሰብአዊ ፍጡሮች ድምፅ መሆን ዘረኝነት ወይም ጠባብነት አይደለም። በመሆኑም የዐማራው ተወላጆች ብቻ ሣይሆኑ፤ ለሰብአዊነት የቆሙ ሁሉ ለዚህ ነገድ ድምፅ ከመሆን አልፈው፣ በኢትዮጵያውያን ላይ ይህን ዓይነት የከፋ ወንጀል የሚፈፅሙትን ለፍትኅ አደባባይ ለማቅረብ ለተያያዝነው ትግል፥ የመረጃ፣ የምክር፣ የዕውቀት እና የገንዘብ ልገሣ እንድታደርጉልን በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን።


No comments:

Post a Comment