Friday, July 15, 2016

በምስራቅ ኢትዮጵያ ያለው የርሃብ አደጋ አሁንም አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንዳለ ኦክስፋም አስታወቀ



ሐምሌ ፰ ( ስምንት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን በላይ ዜጎች አፋጣኝ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ኦክስፋምን ገልጾ፣ ባለፈው ዓመት ዝናብ አለመጣሉን ተከትሎ ሰብልቻቸው የወደሙባቸው አርሶአደሮችና የቤት እንስሶቻቸው ያለቁባቸው አርብቶ አደሮች ምጽዋት ጠባቂ ሆነዋል ብሎአል።

ከድሬደዋ 75 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ፊዲቶ የመጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙት 10ሽህ በላይ ተረጅዎች ሲኖሩ የርሃቡ ተጠቂዎች ውስጥ ሕጻናት መኖራቸውንና በተመጣጠነ የምግብ እጥረት ሳቢያ ክፉኛ እንደተጎዱም ሪፖርቱ አመላክቷል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብና ግብረሰናይ ድርጅቶች የኢትዮጵያ ድርቅ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑን ቢናገሩም ገዥው መንግስት ግን ሁኔታዎችን ማስተባበል መምረጡን ችግሩን ማባባሱን ቲአርቲ ሲቲዝን ዘግቧል። ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይኦኤም በበኩሉ በኢትዮጵያ የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ ከ630 ሽህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ብቻ ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸውን አስታውቋል።

No comments:

Post a Comment